ጌታዬን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን (Gietayien Yagegnehu Qen) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን

ሃይማኖት ፡ አለኝ ፡ ስል ፡ ስገበዝ ፡ ከርሜ (፪x)
መጠውለጉን ፡ ሳላውቅ ፡ ቅጠል ፡ አገልድሜ (፪x)
እርቃኔ ፡ ሲገለጥ ፡ እፍረት ፡ ያዘኝና (፪x)
ወደ ፡ ጌታ ፡ ሮጥኩኝ ፡ መሃሪ ፡ ነውና

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን

ሰው ፡ በእህል ፡ አይጠግብም ፡ ውሃም ፡ አያረካው (፪x)
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ በፍቅር ፡ ካልነካው (፪x)
ጤና ፡ ነኝ ፡ እያለ ፡ እራሱን ፡ ያስታል (፪x)
ቀን ፡ ቀን ፡ በሳቀበት ፡ ማታ ፡ ያቃስታል

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን

ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ይመስል ፡ በከንቱ ፡ ስኮፈስ (፪x)
ቀራንዮን ፡ ትቼ ፡ ታቹን ፡ ስመላለስ (፪x)
ጫማዬን ፡ ስጨርስ ፡ በሸለቆ ፡ ድንጋይ (፪x)
የመለኮት ፡ ጥሪ ፡ መጣልኝ ፡ ከሰማይ

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን

አልጋዬ ፡ ቆርቋሪ ፡ እንቅልፍ ፡ የማይሰጠኝ (፪x)
ምንድነው ፡ እንደዚህ ፡ የሚያገላብጠኝ (፪x)
እያልኩኝ ፡ ስመረር ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰ (፪x)
የሰላም ፡ አሸንዳ ፡ በላዬ ፡ አፈሰሰ

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን

ቀኒቷም ፡ ትባረክ ፡ ጌታን ፡ ያየሁባት (፪x)
ከዘመናት ፡ እስር ፡ የተፈታሁባት (፪x)
የምስራች ፡ ያለኝም ፡ እርሱን ፡ ጌታ ፡ ይክፈለው (፪x)
ጌታ ፡ እኔን ፡ ሲሸልም ፡ ለእርሱም ፡ አክሊል ፡ አለው (፪x)

አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ
ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ
የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን
ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን