ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ነው (Gietayie Bante New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)

ከታላላቆች ፡ ከአለቆች ፡ ጋራ
ፊት ፡ ለፊት ፡ ቆሜ ፡ እኩል ፡ ላወራ
ስለሆንክልኝ ፡ ግርማ ፡ ሞገሴ
ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)

አድነኸኛል ፡ ከሰቆቃዬ
በአንተ ፡ መጽናናት ፡ ደርቋል ፡ እንባዬ
አቁመኸኛል ፡ በተራራ ፡ ላይ
አብቅተኸኛል ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)

በአንተ ፡ ለምልሟል ፡ ምድረ ፡ በዳዬ
በረከት ፡ ሞልቷል ፡ የሕይይወት ፡ ጓዳዬ
ላይ ፡ ታች ፡ ከማለት ፡ ከሩጫ ፡ አርፌ
መብላት ፡ ጀመርኩኝ ፡ እሸት ፡ ቀጥፌ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)

ዛሬስ ፡ ጠላቴ ፡ ሥፍራውን ፡ ለቋል
ከላይ ፡ የነበር ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ ወድቋል
በአንተ ፡ ጀግንነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁኝ
አንተ ፡ ስትከብር ፡ እኔም ፡ ከበርኩኝ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና
እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና
እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል
ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)