ጌታ ፡ ተባረክ (Gieta Tebarek) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ
አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ

ጠራኸኝ ፡ ከዚህ ፡ ክፉ ፡ ዓለም
ነፍሴን ፡ አዳንካት ፡ ዘለዓለም
ከዚህ ፡ የበለጠ ፡ ደስታ ፡ ምንም ፡ የለም
ይኸው ፡ ሞላልኝ ፡ ስለቴ
ክበር ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በህይወቴ
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይዋል ፡ መላው ፡ እኔነቴ

አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ
አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ

በክቡር ፡ ደምህ ፡ አንጽተህ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቀብተህ
አገልጋይ ፡ አረግኸኝ ፡ ጸጋን ፡ ከላይ ፡ ሞልተህ
ለስምህ ፡ ክብር ፡ ልዘምር ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ልጨምር
ላቆምኸኝ ፡ ላምላኬ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ክብር

አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ
አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ

ጠላት ፡ ቢነሳ ፡ በአመጻ ፡ ቢወረውርም ፡ ፍላጻ
ቆምኩኝ ፡ እስከዛሬ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ
ክረምት ፡ ከበጋ ፡ አለፈ ፡ ቃልኪዳንህ ፡ መች ፡ ታጠፈ
አንተን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ሲያይ ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፈ

አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ
አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ

የሶሪያ ፡ ንጉሥ ፡ ደማስቆ
ሴራ ፡ ተንኮሉን ፡ ማን ፡ አውቆ
አልሞ ፡ ነበር ፡ ሊይዘኝ ፡ አሾልቆ
አንተ ፡ ግን ፡ አታጣ ፡ መላ
ለባሪያህ ፡ ሆንኸኝ ፡ ከለላ
አተምከው ፡ ዙሪያዬን ፡ በእሳት ፡ ሰረገላ

አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ
አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ