ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ (Dekamien Ansa Kelayie) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ
ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ግብረ ፡ ጉንዳን ፡ መኖዋን ፡ በበጋ ፡ አሰናድታ
ክረምት ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ትበላለች ፡ ተኝታ
ጻድቅ ፡ በምቹ ፡ ጊዜ ፡ በአንተ ፡ ፊት ፡ ከተጋ
ዋስትና ፡ አለውና ፡ ይኖራል ፡ ምንም ፡ ሳይሰጋ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ
ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ካልተጠበቀ ፡ መንጋ ፡ ማነው ፡ ወተት ፡ የሚሻ?
ያልዘሩትን ፡ ለማጨድ ፡ አይኬድም ፡ ወደ ፡ እርሻ
ጥያቄ ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ እምነቴ ፡ እንዳይከዳኝ
ዛሬ ፡ ቀን ፡ ሳለ ፡ ጌታ ፡ ፍቃድህን ፡ ልፈጽም ፡ እርዳኝ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ
ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ትጥቄን ፡ ሳላጠባብቅ ፡ እንዲያው ፡ መሮጥ ፡ ካሰኘኝ
ተጠልፌ ፡ ወድቄ ፡ ጠላት ፡ እንዳያገኘኝ
ዛሬ ፡ ስራኝ ፡ በጓዳ ፡ በአደባባይም ፡ አይደል
ኋላ ፡ አያቅተኝም ፡ በአንድ ፡ ጠጠር ፡ ሺህ ፡ መግደል

አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ
ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ከተከፈተ ፡ ሰማይ ፡ ወርቃማ ፡ ቅባት ፡ ፈሶ
ጸጋህ ፡ በውስጤ ፡ ይሙላ ፡ መንፈሴን ፡ አረስርሶ
ደዌን ፡ እገስጻለሁ ፡ መናፍስትን ፡ አዛለሁ
ጭፍሮችን ፡ አባርሬ ፡ ምርኮን ፡ እበዘብዛለሁ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ
ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)