በዚህ ፡ ዘመን (Bezih Zemen) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አስተዋይ ፡ የሚሆን ፡ ዝም ፡ ይላሉ (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አብዛልን ፡ ማስተዋል

ኃጥያት ፡ በትር ፡ ይዞ ፡ ኦሆሆ ፡ አደባባይ ፡ ወጣ ፡ አሃሃ
የሚቃወሙትን ፡ እኽኽ ፡ በችጋር ፡ ሊቀጣ ፡ አሃሃ
ክፉዎች ፡ ሲደላቸው ፡ ኦሆሆ ፡ ጻድቃን ፡ ሲቸገሩ ፡ አሃሃ
ተገለባበጠ ፡ እኽኽ ፡ እንዴት ፡ ነው ፡ ነገሩ

አዝ፦ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አስተዋይ ፡ የሚሆን ፡ ዝም ፡ ይላሉ (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አብዛልን ፡ ማስተዋል

ሃሰት ፡ ሲደራርብ ፡ እኽኽ ፡ በሹመት ፡ ላይ ፡ ሹመት ፡ አሃሃ
እውነት ፡ ተናጋሪ ፡ እኽኽ ፡ ጠላት ፡ ሲበዛበት ፡ እኽኽ
ደሆች ፡ ሲነቀሉ ፡ ኦሆሆ ፡ ከቤት፡ ከርስታቸው ፡ እኽኽ
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ አምላክ ፡ አሃሃ ፡ ተሟገትላቸው ፡ አሃሃ

አዝ፦ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አስተዋይ ፡ የሚሆን ፡ ዝም ፡ ይላሉ (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አብዛልን ፡ ማስተዋል

አውሬው ፡ ሲያቆጠቁጥ ፡ እኽኽ ፡ ሥሩን ፡ ሲዘረጋ ፡ አሃሃ
ሃሰተኛው ፡ መሲሕ ፡ እኽኽ ፡ አጃቢ ፡ ሲያንጋጋ ፡ አሃሃ
ጊዜውን ፡ ካልመረመርን ፡ ዘመኑን ፡ ካልዋጀን ፡ አሃሃ
የተወሰድን ፡ እንደሆን ፡ ኦሆሆ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ ሊበጀን ፡ አሃሃ

አዝ፦ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አስተዋይ ፡ የሚሆን ፡ ዝም ፡ ይላሉ (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አብዛልን ፡ ማስተዋል

መዝናናት ፡ አበዛን ፡ እኽኽ ፡ መዋጋት ፡ ትተናል ፡ አሃሃ
ያለነው ፡ ጦር ፡ ሜዳ ፡ አሃሃ ፡ መሆኑን ፡ ረስተናል ፡እኽኽ
እስኪ ፡ እንበርከክ ፡ እኽኽ ፡ ወደ ፡ እልፍኝ ፡ እንግባ ፡ እኽኽ
ሰይጣን ፡ ጸሎት ፡ እንጂ ፡ አሃሃ ፡ አይፈራም ፡ ጭብጨባ ፡ አሃሃ

አዝ፦ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አስተዋይ ፡ የሚሆን ፡ ዝም ፡ ይላሉ (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አብዛልን ፡ ማስተዋል