ባነበብነው ፡ በሰማነው (Banebebnew Besemanew) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ
ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ

እነዚህን ፡ የሚያህሉ ፡ ምስክሮች ፡ አሉ ፡ በዙሪያችን
እኛም ፡ ደግሞ ፡ ሃያል ፡ ክንድህ ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ አይተናል ፡ በዓይናችን
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ከምንልህ ፡ በላይ
ሥምህ ፡ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ በምድር ፡ በሰማይ
(፪x)

አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ
ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ

በነፍሳችን ፡ እንዳንዝል ፡ እንዳንደክም ፡ ደግፎ ፡ የሚያቆመን
ለአንድ ፡ አፍታም ፡ የማንረሳው ፡ የማንጥለው ፡ ድንቅ ፡ ታሪክ ፡ አለን
የነገው ፡ ደመና ፡ የሚያጨልመው ፡ ነገር
አይከለክለንም ፡ አንተን ፡ ከማመስገን
(፪x)

አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ
ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ

አይተንሃል ፣ ሰምተንሃል ፣ ዳሰንሃል ፣ እንመሰክራለን
እንደ ፡ ጠላታችን ፡ ምኞት ፡ አልጠፋንም ፡ ዛሬም ፡ በሕይወት ፡ አለን
በሆነልን ፡ ነገር ፡ ብዙ ፡ ተደንቀናል
የአባታችን ፡ መንግሥት ፡ ገና ፡ ይጠብቀናል
(፪x)

አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ
ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ

ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ እውነተኛ ፣ ፊትን ፡ አይተህ ፡ ፈጽሞ ፡ አታደላ
ፀሐይ ፡ ለጠለቀችበት ፡ ለጨነቀው ፣ ትሰጣለህ ፡ መላ
ጊዜ ፡ ደረሰና ፡ ሁሉም ፡ ልኩ ፡ ታውቋል
የሳቀ ፡ ሲያለቅስ ፣ ያለቀሰም ፡ ስቋል
(፪x)

አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ
ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ