From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ለአሉባልታ ፡ ጊዜ ፡ የለኝ ፡ እኔ
አውርቼ ፡ አልጨረስኩ ፡ ስለመዳኔ
አልጣላ ፡ ሁሉም ፡ የመጣው ፡ ከአንተ ፡በኋላ
በመቦጫጨቅ ፡ ባርኮት ፡ አይመጣ
ለውኃ ጥማት ፡ ውኃ አይጠጣ
እስኪ ፡ እንጨብጥ ፡ እርፍ ፡ ማረሻ
ሥራ ፡ ነውና ፡ የአገር ፡ መነሻ ፡ አሀ ፡ አሀ
አርሰን ፡ ሳንዘራ ፡ መስከረም ፡ ጠባ
አገር ፡ በወሬ ፡ አትገነባ
ነገም ፡ እንዳያልፍ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ
ጉልበት ፡ ማንቃቱ
ከአየር ፡ ከውሃው ፡ ምንም ፡ አላጣን
ስላልሰራን ፡ ነው ፡ ረሃብ ፡ የቀጣን
የሞተው ፡ ሞቶ ፡ ያለነው ፡ አለን
ታጥቀን ፡ ከወጣን ፡ ነገ ፡ እንደርሳለን ፡ አሀአሀ
መስመር ፡ ጠብቆ ፡ ሮጦ ፡ ማሸነፍ
ወይስ ፡ በተንኮል ፡ ወንድምን ፡ መጥለፍ
የትኛው ፡ ይሆን ፡ የተፈቀደው
እኔ ፡ ትቻለሁ ፡ ህሊና ፡ ይፍረድ
እጣ ፡ የደረሰው ፡ ትላንት ፡ ተገፋ
ዛሬስ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ ባለወረፋ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እየን ፡ ከሰማይ
የፍቅር ፡ ዘይት ፡ አፍስስ ፡ በእኛ ፡ ላይ
የወሬ ፡ ጠላት ፡ ሥራን ፡ አፍቃሪ
በውኃ በየብስ ፡ በአየር ፡ በራሪ
የትውልድ ፡ ኩራት ፡ መድሃኒተኛ
አምላካችን ፡ ሆይ ፡ አምጣልን ፡ ለእኛ
|