Tamrat Haile/Egziabhier Terarayien Anagerew/Andun Seneshegnew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ታምራት ሃይሌ ርዕስ አንዱን ስንሸኘው አልበም እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው

አዝ የዚህ ዓለም ኑሮ ምድረበዳ የማይደፈን ቀዳዳ ቋጡ ጠብ አላለም ጉድጓዱም አልሞላ አንዱን ስንሸኘው ከተፍ ይላል ሌላው እንቆቅልሹ ሺህ ችግሩም እልፍ ነው ጌታን አምነን እርፍ ነው ጌታን ይዘን እርፍ ነው ጌታ ካለ እርፍ ነው

ልንደላደል ልንመቻች ቀን ሙሉ ስንሮጥ እላይ እታች መቼ ሞላልን እንዲህ እየጣርን ነፍሳችን እረፍት አጥታ ፀሐይ ማዘቅዘቋን መምሸቱን አውቀን ወደ እግዚአብሄር ጉያ እንግባ ፈጥነን

አዝ የዚህ ዓለም ኑሮ ምድረበዳ የማይደፈን ቀዳዳ ቋጡ ጠብ አላለም ጉድጓዱም አልሞላ አንዱን ስንሸኘው ከተፍ ይላል ሌላው እንቆቅልሹ ሺህ ችግሩም እልፍ ነው ጌታን አምነን እርፍ ነው ጌታን ይዘን እርፍ ነው ጌታ ካለ እርፍ ነው

በመሸማቀቅ በሰቀቀን በሃሩር ፀሐይ በእኩለ ቀን ውኃ ፍለጋ ከአድማስ ወዲያ የተጓዘችው በሰማሪያ አምስቱም ባሎቿ ያልሰጧትን ደስታ ኢየሱስን ስታገኝ ቋጠሮዋ ተፈታ

አዝ የዚህ ዓለም ኑሮ ምድረበዳ የማይደፈን ቀዳዳ ቋጡ ጠብ አላለም ጉድጓዱም አልሞላ አንዱን ስንሸኘው ከተፍ ይላል ሌላው እንቆቅልሹ ሺህ ችግሩም እልፍ ነው ጌታን አምነን እርፍ ነው ጌታን ይዘን እርፍ ነው ጌታ ካለ እርፍ ነው

እንድንጮህ አባት አባት ብለን እግዚአብሔር ሰጠን መንፈሱን በሰማይም ቤት ሰርቶልናል በቅርቡም መጥቶ ይወስደናል ወላጅ አልባ ልጆች አይደለንም እኛ ጌታችን በክብር ይመጣል ዳግመኛ

አዝ የዚህ ዓለም ኑሮ ምድረበዳ የማይደፈን ቀዳዳ ቋጡ ጠብ አላለም ጉድጓዱም አልሞላ አንዱን ስንሸኘው ከተፍ ይላል ሌላው እንቆቅልሹ ሺህ ችግሩም እልፍ ነው ጌታን አምነን እርፍ ነው ጌታን ይዘን እርፍ ነው ጌታ ካለ እርፍ ነው

የቤተልሔም ረሃብ ያልፋል ወደ ሞአብስ ምን ያለፋል ያለመጠበቅ ያለማረፍ ለመዘረፍ ነው ለመገፈፍ እግዚአብሔር ሕዝቡን በርግጥ ይጐበኛል ሁሉም ሰው በጊዜው ዳኝነት ያገኛል