የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነው (Yetadele Mesgun New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

 
የሉም ፡ ሲባል ፡ ይኖራሉ (አሁሁሁ) ፡ ጠፉ ፡ ሲባል ፡ ይበዛሉ (ኦሆሆሆ)
ሲዋለዱ ፡ ብዙ ፡ መንታ (አሃሃሃ) ፡ ሩጫቸውን ፡ ማን ፡ ሊገታ (አሃሃሃ)
አይታክቱም ፡ ይሄዳሉ ፡ አይደክሙም ፡ ይበረታሉ
እንደ ፡ ንስር ፡ ይበራሉ ፡ እጥፍ ፡ ድርብ ፡ ያፈራሉ

አዝ:- እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሞት ፡ የጠራው
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ከህዝብ ፡ የዋጀዉ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ህዝቤ ፡ ገንዘቤ ፡ ያለዉ
በዓለም ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በድል ፡ የመራዉ
የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነዉ

በሰው ፡ ብልሃት ፡ የተሰራ (አሃሃሃ) ፡ በሥጋ ፡ ደም ፡ የሚመራ (አሃሃሃ)
ሃስቡን ፡ ለፍልስፍና (አሃሃሃ) ፡ እምነታቸው ፡ መች ፡ ሆነና (አሃሃሃ)
ይናገሩ ፡ ያዳናቸው ፡ እንደ ፡ ሰማይ ፡ ከዋክብት ፡ ናቸው
ዲያቢሎስም ፡ ያውቃቸዋል ፡ ጊዜ ፡ ስጡኝ ፡ ይላቸዋል

አዝ:- እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሞት ፡ የጠራው
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ከህዝብ ፡ የዋጀዉ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ህዝቤ ፡ ገንዘቤ ፡ ያለዉ
በዓለም ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በድል ፡ የመራዉ
የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነዉ

እሳት ፡ አለ ፡ በውስጣቸው (እሄሄው) ፡ ማንም ፡ አይችል ፡ ሊያጠፋቸው (እሄሄው)
አይቻሉም ፡ ሲነኳቸው (እሄሄው) ፡ ተዋጊ ፡ ነው ፡ አምላካቸው (እሄሄው)
ሰባኪዎች ፡ በመገለጥ ፡ ለዲያቢሎስ ፡ እሳት ፡ ረመጥ
ዘማሪዎች ፡ በበገና ፡ ይቀባሉ ፡ ገና ፡ ገና

አዝ:- እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሞት ፡ የጠራው
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ከህዝብ ፡ የዋጀዉ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ህዝቤ ፡ ገንዘቤ ፡ ያለዉ
በዓለም ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በድል ፡ የመራዉ
የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነዉ

ሰይፍ ፡ አይዙም ፡ በእጃቸው (እሄሄው) ፡ የመንፈስ ፡ ነው ፡ መሳሪያቸው (እሄሄው)
እዩት ፡ እስቲ ፡ ይህን ፡ ምርኮ (ኦሆሆሆ) ፡ መንገደኛ ፡ አይደለም ፡ እኮ (ኦሆሆሆ)
የክርስቶስ ፡ ስም ፡ ያዳነው ፡ የካህናት ፡ መንግሥት ፡ ነው
የዓለም ፡ ብርሃን ፡ የምድር ፡ ጨው ፡ እንደ ፡ ከዋክብት ፡ የተረጨው

አዝ:- እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሞት ፡ የጠራው
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ከህዝብ ፡ የዋጀዉ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ህዝቤ ፡ ገንዘቤ ፡ ያለዉ
በዓለም ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በድል ፡ የመራዉ
የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነዉ

ሟርት ፡ አይሰራም ፡ በእስራኤል ፡ ላይ (አሃሃሃይ) ፡ አስማት ፡ የለም ፡ በያዕቆብ ፡ ላይ (ይሄሄሄይ)
አይቆጠርም ፡ ብዛቱ (ዑሁሁሁ) ፡ ድንበር ፡ የለው ፡ ለግዛቱ (ዑሁሁሁ)
እግዚአብሔር ፡ እፍ ፡ ያለበት ፡ የፈጠረው ፡ ለበረከት
መድሃኒት ፡ ነው ፡ መፈወሻ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ መጨረሻ

አዝ:- እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሞት ፡ የጠራው
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ከህዝብ ፡ የዋጀዉ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ህዝቤ ፡ ገንዘቤ ፡ ያለዉ
በዓለም ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በድል ፡ የመራዉ
የታደለ ፡ ምስጉን ፡ ነዉ