የእግዚአብሔርን ፡ ማዳን (YeEgziabhieren Madan) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

 
አዝ:- ተራራው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ሸለቆው ፡ ከፍ ፡ ይበል
ስርጓጎጡም ፡ ሜዳ ፡ ይሁን ፡ ጠማማውም ፡ ይቅና
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ እንዲያይ

የአዋጅ ፡ ነጋሪው ፡ ድምጽ ፡ ሳይታክት ፡ ይጮሃል
መንገድን ፡ በበረሃ ፡ አስተካክሉለት ፡ ይላል
ልባችንን ፡ አናደንድን ፡ አይልበስ ፡ ጆሮ ፡ ዳባ
በሮችን ፡ ክፈቱለት ፡ የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ይግባ

አዝ:- ተራራው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ሸለቆው ፡ ከፍ ፡ ይበል
ስርጓጎጡም ፡ ሜዳ ፡ ይሁን ፡ ጠማማውም ፡ ይቅና
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ እንዲያይ

ማዳኑ ፡ እንዳይገለጥ ፡ ክንዱ ፡ እንዳይዘረጋ
ብዙ ፡ እንቅፋት ፡ አለ ፡ እኔና ፡ እናንተ ፡ ጋር
የድካሙ ፡ ሸለቆ ፡ የትዕቢት ፡ ኮረብታ
ከልክሎት ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ክብሩን ፡ እንዳይገልጥ ፡ ጌታ

አዝ:- ተራራው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ሸለቆው ፡ ከፍ ፡ ይበል
ስርጓጎጡም ፡ ሜዳ ፡ ይሁን ፡ ጠማማውም ፡ ይቅና
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ እንዲያይ

ጆሮዎቹ ፡ ከመስማት ፡ መቼም ፡ አልደነቆሩም
ከማዳን ፡ ከመፈወስ ፡ እጆቹስ ፡ መቼ ፡ አጠሩ
እንደ ፡ ግድግዳ ፡ ሆኖ ፡ ኀጢአት ፡ ነው ፡ የለየን
የተገባልን ፡ ተስፋ ፡ በሙላት ፡ መቼ ፡ አየን

አዝ:- ተራራው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ሸለቆው ፡ ከፍ ፡ ይበል
ስርጓጎጡም ፡ ሜዳ ፡ ይሁን ፡ ጠማማውም ፡ ይቅና
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ እንዲያይ

ጠላትን ፡ አሳልፎ ፡ በእጃችን ፡ ሊሰጠን
መንፈሱን ፡ ሊያፈስልን ፡ ሊሰራን ፡ ሊለውጠን
የሰራዊቱ ፡ ጌታ ፡ ያልፋል ፡ በሰፈራችን
በንሰሃ ፡ እንውደቅ ፡ በደሙ ፡ ይንፃ ፡ ጓዳችን

አዝ:- ተራራው ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ሸለቆው ፡ ከፍ ፡ ይበል
ስርጓጎጡም ፡ ሜዳ ፡ ይሁን ፡ ጠማማውም ፡ ይቅና
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ እንዲያይ