From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ወዳጄ ፡ አብርሃም ፡ ፊቴ ፡ ተመላለስ
እኔን ፡ አይገደኝም ፡ ኪዳኔን ፡ ለማደስ
እድሜ፡ ሮጦ ፡ ሮጦ ፡ ቢደርስ ፡ ጫፍ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ያልፋል ፡ የኔ ፡ ቃል ፡ አያልፍም
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
የማያልፍ ፡ ምን ፡ አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከረዳ
የእምነት ፡ ምንጭ ፡ ይሆናል ፡ ይሄ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ያለው ፡ ይሄድና ፡ ደግሞ ፡ ይመጣል ፡ ሌላ
ግዙፉ ፡ ተራራ ፡ ይሆናል ፡ ደልዳላ
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
የመለኮት ፡ አዋጅ ፡ ከመታ ፡ ከሰማይ
ኢየሱስ ፡ ከአዘዘ ፡ ይኬዳል ፡ ውኃ ፡ ላይ
ሙታን ፡ ይነሳሉ ፡ እስራት ፡ ይፈታል
ቁራሹ ፡ ተባርኮ ፡ ሺሆች ፡ ይበሉታል
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
ጌድዮንና ፡ ባርቅ፡ ዮፍታሄና ፡ ሳምሶን
ሳሙኤልና ፡ ዳዊት ፡ ጳውሎስና ፡ ጴጥሮስ
የአንበሳን ፡ አፍ ፡ ዘጉ ፡ እሳት ፡ አልበላቸው
ለታማኝነቱ ፡ ምስክሮች ፡ ናቸው
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
ምድያም ፡ በረሃ ፡ በፀሐይ ፡ ቃጠሎ
በቁጥቋጦ ፡ እሳት ፡ ራዕይ ፡ አቀብሎ
የፈርዖንን ፡ ክንድ ፡ በመቅሰፍት ፡ አድቅቆ
አሻግሮ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ህዝቡን ፡ አስለቅቆ
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
ጉድጓዱን ፡ ቆፍረህ ፡ ውኃ ስጣወጣ
ዞርበል ፡ የኔ ፡ ነው ፡ ባይ ፡ ምቀኛ ፡ ቢመጣ
እልፍ ፡ ብለህ ፡ ቆፍር ፡ ከሰው ፡ አትጣላ
ርሆቦት ፡ ይሆናል ፡ የኋላ ፡ የኋላ
አዝ:- ታማኝ (፫x)
ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ በቃሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ እልል ፡ ይበሉ (፪x)
|