ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አሳረፈኝ (Menchun Kefto Asarefegn) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)

እኔም ፡ እንደ ፡ አጋር ፡ ተሰድጃለሁ
በምድረ ፡ በዳ ፡ ተቅበዝብዣለሁ
ዐይኔን ፡ ቢከፍተው ፡ ሰጥቶኝ ፡ ማስተዋል
ለካስ ፡ ከጐኔ ፡ የውኃ ፡ ምንጭ ፡ ኖሯል

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)

በእኩለ ፡ ቀን ፡ በፀሐይ ፡ ንዳድ
መመላለሱ ፡ ከያዕቆብ ፡ ጉድጓድ
ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ እፎይ ፡ ብያለሁ
የሕይወትን ፡ ምንጭ ፡ ጌታን ፡ አገኘሁ

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)

ታሪክን ፡ ለዋጭ ፡ ተአምር ፡ ሰሪ
እስራት፡ ፈቺ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ
በምክር ፡ ታላቅ ፡ በስራ ፡ ብርቱ
ወደር ፡ የሌለው ፡ ለጌትነቱ

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)

ተቅበዝባዧ ፡ በግ ፡ በረት ፡ የሌላት
ነጣቂ ፡ ተኩላ ፡ የተከተላት
አዳኝ ፡ ታድኖ ፡ ታዳኙ ፡ ድኖ
ይኸው ፡ አየነው ፡ ስልጣን ፡ ተክኖ

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)

የሟርት ፡ የመተት ፡ የባዕድ ፡ አምልኮ
የጨለማው ፡ ሃይል ፡ ሰፈር ፡ ታውኮ
እስረኛው ፡ ወጣ ፡ ከግዞት ፡ አገር
የአምላኩ ፡ ዝና ፡ ለዓለም ፡ ይነገር

አዝ:- የህይወት ጥማት ፡ አንገብግቦኝ ፡ ብዙ ፡ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፡ ፍለጋ ፡ተንከራተትኩ
በበረሃ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ ጌታ ፡ አገኘኝ
ምንጩን ፡ ከፍቶ ፡ አጠጥቶ ፡ አሳረፈኝ (፪x)