ለጥቂት ፡ ጊዜ (Leteqit Gizie) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

 
አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)

በመላክት ፡ አጀብ ፡ በእግዚአብሔር ፡ መለከት
ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ከላይ ፡ ከሰማያት
የአባቴ ፡ ብሩካን ፡ ኑ ፡ እረፉ ፡ ይለናል
እንደ ፡ ድካማችን ፡ ዋጋ ፡ ይከፍለናል
ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ
እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ

አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)

በጌታ ፡ የሞቱ ፡ ቀድመው ፡ ይነሳሉ
ሰማያዊ ፡ አካል ፡ ፈጥነው ፡ ይለብሳሉ
እኛ ፡ ሕያዋን ፡ እንለወጣለን
አብረን ፡ በደመና ፡ እንነጠቃለን
ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ
እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ

አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)

ዓለም ፡ በክፋቷ ፡ እየባሰች ፡ ሄደች
ሕያዋንን ፡ አልፋ ፡ በድን ፡ አሳደደች
አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ነው ፡ እንደተጻፈው
በክርስቶስ ፡ ትዕግስት ፡ ሁሉን ፡ እንለፈው
የሚረዳን ፡ ጸጋ ፡ ጌታ ፡ ይሰጠናል
ኋላም ፡ በመምጣቱ ፡ በክብር ፡ ይገልጠናል

አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)

ጌታ ፡ የሚዘገይ ፡ መስሎ ፡ ቢታያቸው
በዚህ ፡ ዓለም ፡ አምላክ ፡ ታውሮ ፡ ዐይናቸው
እንደ ፡ ተስፋ ፡ ቃሉ ፡ አይዘገይም ፡ በእውነት
እንደ ፡ ሌባ ፡ ሆኖ ፡ ይመጣል ፡ በድንገት
የወጉት ፡ ያዩታል ፡ በዘውድ ፡ አሸብርቆ
በግርማው ፡ ሲገለጥ ፡ ከከዋክብት ፡ ደምቆ

አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)

ነቀፋና ፡ ስድብ ፡ ስደትና ፡ ዛቻ
የጠላት ፡ ተግዳሮት ፡ የዘመድ ፡ ጥላቻ
እጦትና ፡ ህመም ፡ ሃዘንና ፡ እሮሮ
ያለው ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉም ፡ ተደምሮ
ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ሰማያዊ ፡ ክብር
ያሁን ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ አይወዳደር

አዝ:- ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን
በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን (፪x)