From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ቃሉ ፡ ሲያስተምረን ፡ መንፈሱ ፡ ሲያጽናናን
ካቻምናን ፡ አለፍን ፡ ተሻገርን ፡ አምናን
ጠላት ፡ ቢቃወመን ፡ እጅግ ፡ ተገዳድሮ
ጌታ ፡ ተዋግቶልን ፡ ደረስን ፡ ዘንድሮ (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
መጻተኞች ፡ ብንሆን ፡ ምድር ፡ ያልተገባን
ምንም ፡ አልጐደለን ፡ ለእኛ ፡ ከሚረባን
ወላጅ ፡ እንደሌለው ፡ ልጅ ፡ አላደረገን
የሁላችን ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ጉንድሹ ቢመጣ ፡ አካሉ ፡ ተሟልቶ
እውሩ ፡ ቢመጣ ፡ ሄደ ፡ ዓይኑ ፡ ተከፍቶ
ሙታን ፡ ተነስተዋል ፡ የተራቡም ፡ በሉ
እጁን ፡ ከዘረጋ ፡ ይደርሳል ፡ ለሁሉ (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
ሕዝቡ ፡ እንደሆነ ፡ አይቀር ፡ ተስፋውን ፡ መውረሱ
ፈርዖን ፡ ለምን ፡ ነው ፡ ኃይሉን ፡ መጨረሱ
ባሕር ፡ ተከፈለ ፡ በድል ፡ ተሻገሩ
አንዴ ፡ እስከዘለዓለም ፡ ተሰብሯል ፡ ቀንበሩ (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
|