From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በአንድነት ፡ አስሮ ፡ በፍቅር ፡ ባርኮ
ይስብስብልህ ፡ ምርኮ ፡ በምርኮ
ብዛ ፡ ተባዛ ፡ የአባቴ ፡ መንጋ
ይሚነሳብህ ፡ ወገብ ፡ ይወጋ
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ ፡ ይጠብቅህ
ፊቱን ፡ ደግሞ ፡ ያብራልህ ፡ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፡ ፊቱን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ያንሳ
ሰላሙን ፡ ደግሞ ፡ ይስጥህ ፡ ይጨምርልህ
የጽድቅን ፡ ኑሮ ፡ የቅድስናን
እያበዛልህ ፡ ጸሎት ፡ ጽሞናን
የቃሉን ፡ ረሃብ ፡ የአምልኮን ፡ ጥማት
ያትረፍርፍልህ ፡ ቅባት ፡ በቅባት
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ ፡ ይጠብቅህ
ፊቱን ፡ ደግሞ ፡ ያብራልህ ፡ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፡ ፊቱን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ያንሳ
ሰላሙን ፡ ደግሞ ፡ ይስጥህ ፡ ይጨምርልህ
ሽማግሌዎች ፡ ከአደባባይ
ህጽናት ፡ ልጆች ፡ ከሜዳው ፡ ላይ
የአዝመራው ፡ መዓዛ ፡ የአምልኮ ፡ መድረክ
ሁሉም ፡ ይለምልም ፡ ሁሉም ፡ ይባረክ
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ ፡ ይጠብቅህ
ፊቱን ፡ ደግሞ ፡ ያብራልህ ፡ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፡ ፊቱን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ያንሳ
ሰላሙን ፡ ደግሞ ፡ ይስጥህ ፡ ይጨምርልህ
የግብጽ ፡ ቁስል ፡ ደዌ ፡ ቸነፈር
ጭንገፋና ፡ ሞት ፡ አንተን ፡ አይድፈር
ቀሳፊው ፡ መልአክ ፡ ቤትህ ፡ አይግባ
ጉበን ፡ መቃንህ ፡ በደሙ ፡ ይቀባ
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ ፡ ይጠብቅህ
ፊቱን ፡ ደግሞ ፡ ያብራልህ ፡ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፡ ፊቱን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ያንሳ
ሰላሙን ፡ ደግሞ ፡ ይስጥህ ፡ ይጨምርልህ
ተምች ፡ አይውረር ፡ ደግሞም ፡ ኩብኩባ
የአየር ፡ ንብረትህ ፡ እንዳይዛባ
ወንዝ ፡ አፈርህ ፡ ጌታ ፡ ይባርክልህ
ቁርባን ፡ መስዋዕትህን ፡ ያለምልምልህ
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ ይባርክህ ፡ ይጠብቅህ
ፊቱን ፡ ደግሞ ፡ ያብራልህ ፡ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፡ ፊቱን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ያንሳ
ሰላሙን ፡ ደግሞ ፡ ይስጥህ ፡ ይጨምርልህ
|