From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ስራችንን ፡ ይመዝናል ፡ ዋጋችንን ፡ ይተምናል
ከፋኝ ፡ ብለን ፡ አናጉረምርም ፡ ስለሁሉ ፡ እናመስግነው
ደላኝ ፡ ብለን ፡ አንታበይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
ቃልን ፡ ለመናገር ፡ አንደበት ፡ ቸኩሎ
ሲያነሳ ፡ ሲጥል ፡ ባልዋሉበት ፡ ውሎ
ለምን ፡ እናፍራለን ፡ በተናገርንበት
እርሱ ፡ ያደላድላል ፡ ሁሉንም ፡ ተውለት
ሃሰት ፡ ሲሆን ፡ እውነት ፡ ያልነው
ጸድቆ ፡ ሲገኝ ፡ የኮንነው
አንተ ፡ ያልነው ፡ ሲሆን ፡ አንቱ
ለእኛ ፡ ሚቀረን ፡ ትዝብቱ
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ስራችንን ፡ ይመዝናል ፡ ዋጋችንን ፡ ይተምናል
ከፋኝ ፡ ብለን ፡ አናጉረምርም ፡ ስለሁሉ ፡ እናመስግነው
ደላኝ ፡ ብለን ፡ አንታበይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
ፍሬ ፡ የሌለባት ፡ የደረቀች ፡ ዛፍ
እያሉ ፡ ገረፏት ፡ ስታገድም ፡ ስታልፍ
ኋላም ፡ ሰባት ፡ ወልዳ ፡ ምስኪን ፡ መካኒቱ
የተባለው ፡ ሁሉ ፡ መና ፡ ሲሆን ፡ ከንቱ
ልዑል ፡ አምላክ ፡ ከፍ ፡ ሲያደርጋት
ቢንጠራሩ ፡ ላይደርሱባት
አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ብላ ፡ ተቀኘች ፡ በመዝሙር
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ስራችንን ፡ ይመዝናል ፡ ዋጋችንን ፡ ይተምናል
ከፋኝ ፡ ብለን ፡ አናጉረምርም ፡ ስለሁሉ ፡ እናመስግነው
ደላኝ ፡ ብለን ፡ አንታበይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
ፈተና ፡ በዝቶብን ፡ ብናዝን ፡ ብንከፋ
ቢወሳሰብብን ፡ ውሉ ፡ እስከሚጠፋ
ሚስጥሩ ፡ የአምላክ ፡ ነው ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ በእጁ
የተገለጠው ፡ ግን ፡ ለእኛ ፡ ለልጆቹ
ሁሉን ፡ ሲያደርግ ፡ የለን ፡ በጐ
ሲያበጃጀው ፡ ውብ ፡ አድርጐ
እናያለን ፡ የእርሱን ፡ ማዳን
እንድንጸና ፡ ጌታ ፡ ይርዳን
አዝ:- እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ስራችንን ፡ ይመዝናል ፡ ዋጋችንን ፡ ይተምናል
ከፋኝ ፡ ብለን ፡ አናጉረምርም ፡ ስለሁሉ ፡ እናመስግነው
ደላኝ ፡ ብለን ፡ አንታበይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው
|