አድራሻዬ ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው (Adrashayie Mesqelu Ser New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

 
በእንባና ፡ በጣር ፡ በጭንቅ ፡ በመከራ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አልፎ ፡ ሕይወቴ ፡ ተገራ
ማዕበሉም ፡ ንፋሱም ፡ ሰራኝ ፡ ደህና ፡ አድርግ
ጠላት ፡ ለክፉ ፡ ሲል ፡ ሆነልኝ ፡ ለበጐ

ዛሬማ ፡ ወዳጄ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተከፍተው ፡ አያለሁ ፡ አርቄ
የሕይወት ፡ ትርጉሙ ፡ በወጉ ፡ ገብቶኛል
እይዛለሁ ፡ አጥብቂ ፡ አድራሻዬን

አዝ:- አድራሻዬ ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ ፡ መጽናናዬ ፡ መፈወሻዬ
መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ

የብሶት ፡ የቋቱም ፡ ሲገነፍል ፡ ሞልቶ
እምነቴ ፡ ሲከዳኝ ፡ መታጠቂያው ፡ ላልቶ
የመለወጫዬ ፡ የጸሎቴ ፡ ቦታ
ድምጹን ፡ ሲያሰማኝ ፡ ሲያናግረኝ ፡ ጌታ

እጁ ፡ ስትዳስሰኝ ፡ ሸክሜን ፡ ሲያወርድልኝ ፡ ሁሉን ፡ እረሳለሁ
በሃዘን ፡ መጥቼ ፡ በእምባ ፡ ተንበርክኬ
በሳቅ ፡ እነሳለሁ ፡ አድራሻዬ

አዝ:- አድራሻዬ ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ ፡ መጽናናዬ ፡ መፈወሻዬ
መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ

ንፋሱ ፡ ባይነፍስ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
እጠብቀዋለሁ ፡ ጌታ ፡ ብሏልና
ቃሉ ፡ አይታጠፍም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አምላኬ
ምስክር ፡ ቢያስፈልግ ፡ የትላንት ፡ ታሪኬ

የመጠበቂያዬን ፡ የጸሎቴን ፡ አምባ ፡ አልወጣም ፡ ለቅቄ
እስኪ ፡ መልስልኝ ፡ እማጸነዋለሁ
ከእግሩ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ አድራሻዬ

አዝ:- አድራሻዬ ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ ፡ መጽናናዬ ፡ መፈወሻዬ
መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ

ያወቀ ፡ ይስታል ፡ የቆመም ፡ ይወድቃል
ብልህ ፡ ሰው ፡ ለነገው ፡ ስንቁን ፡ ይሰንቃል
የጭንቀቱ ፡ ጭጋግ ፡ የተስፋውን ፡ ጮራ
ሲሸፍነው ፡ ዋለ ፡ ወሬ ፡ ስናወራ

አሁን ፡ ይበቃናል ፡ ለወሬ ፡ በርትተን ፡ ለጸሎት ፡ መስነፉ
እንግባ ፡ ከጓዳ ፡ እዚያ ፡ ነው ፡ ሚገኘው
የበረከት ፡ ቁልፉ ፡ አድራሻዬ

አዝ:- አድራሻዬ ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ ፡ መጽናናዬ ፡ መፈወሻዬ
መስቀሉ ፡ ስር ፡ ነው ፡ አድራሻዬ