ሰምቶ ፡ የሚመልስ (Semto Yemimeles) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg

፲ ፩
(11)

በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልፍ
(Bedebebeqosh Qenu Endayalf)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ምድር ፡ ለሰው ፡ ልጆች ፡ ተሰጥታለች ፡ አልፋ (፪x)
ሁሉም ፡ በየሙያው ፡ ይላል ፡ ቀና ፡ ደፋ (፪x)
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ አይባል ፡ ከዚያ ፡ በመለስ (፪x)
ቅዱሱ ፡ ይቀደስ ፡ እርኩሱም ፡ ይርከስ (፪x)
አይቶ ፡ ሰምቶ ፡ የለየ ፡ ነጸነት ፡ አለው
እንስበከው ፡ እንጂ ፡ ጡንቻ ፡ አናሳየው
ያሻውን ፡ ይከተል ፡ ሰው ፡ እንደገባው
ሰይፋችን ፡ ይመለስ ፡ ወደ ፡ ሰገባው

አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
(ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)

ምድር ፡ ተባርካለች ፡ በሃይማኖት ፡ ብዛት (፪x)
ህመሟ ፡ ባሰ ፡ እንጂ ፡ አንዱም ፡ አልፈወሳት (፪x)
ምድር ፡ ተባርካለች ፡ በሃይማኖት ፡ ሃብት (፪x)
እንትንና ፡ እንትን ፡ እንትን ፡ በሚሉት (፪x)
አሁንም ፡ ይፈልቃል ፡ በየቀበሌው
እናትና ፡ አባት ፡ አያት ፡ የሌለው
አንዱ ፡ ካላዳነ ፡ አያድንም ፡ ሲሉ
ወገኔ ፡ ተመለስ ፡ ይቅርብህ ፡ እልሁ

አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
(ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)

በስራ ፡ ይገለጥ ፡ የያዝነው ፡ እምነት (፪x)
ሙታንም ፡ ይነሱ ፡ ይውጡ ፡ አጋንንት (፪x)
ዳንኩኝ ፡ ተፈወስኩኝ ፡ ብለው ፡ ይመስክሩ (፪x)
የሃይማኖት ፡ ፋርዳ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ቁም ፡ ነገሩ (፪x)
የሚያድን ፡ እምነት ፡ የሚያደርስ ፡ ሠማይ
ከሌለው ፡ ሰው ፡ አልፎ ፡ ሰርቶ ፡ አይበላም ፡ ወይ
በሰላም ፡ እንደር ፡ አይረበሽ ፡ ሰፈር
ድንበር ፡ አትለፉ ፡ ተዉ ፡ አንደፋፈር

አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
(ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)

ደርሶ ፡ ስም ፡ ለማጥፋት ፡ ወሬ ፡ አሉባልታ (፪x)
ጭራሽ ፡ ይባል ፡ ብሎ ፡ በአስክሬን ፡ ጨዋት (፪x)
ትዳርን ፡ አፋቶ ፡ ልጅ ፡ ከእናት ፡ ነጥሎ (፪x)
ከቀዬ ፡ ከሰፈር ፡ ከማህበር ፡ አግልሎ (፪x)
ከገነት ፡ ሊገባ ፡ እንዲያው ፡ መታሰቡ
ቀርጥህን ፡ እወቀው ፡ አትደርስ ፡ ከአጠገቡ
አሳደህ ፡ እሰረው ፡ ግደልልኝ ፡ ያለ
ዲያቢሎስ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይደለ

አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
(ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)

የእኔ ፡ ይበልጣል ፡ ቢሉ ፡ ምንም ፡ ክፋት ፡ የለው (፪x)
እኛ ፡ ማንስማማው ፡ ዛቻ ፡ ሲጀመር ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለሁሉም ፡ ይበቃል
ምስክር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አያሻው ፡ ጠበቃ (፪x)
እናንት ፡ የአምላክ ፡ ልጆች ፡ ከቶ ፡ አትታወኩ
ሁሉም ፡ በየቋንቋው ፡ ይጩህ ፡ ወደአምላኩ
የሁሉም ፡ ማንነት ፡ በተግባር ፡ ይታያል
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ በእሳት ፡ ይለያል

አዝ፦ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ይንገሥ
ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን
(ወርዶ ፡ የሚያድን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ይሁን)