ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ (Keber Lekeber Geta) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg

፲ ፩
(11)

በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልፍ
(Bedebebeqosh Qenu Endayalf)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ
ውዳሴና ፡ ዕልልታ
አምልኮና ፡ ስግደት
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)

መላዕክት በሠማይ ፡ ያሉ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ
ቀን ፡ የላቸው ፡ ሌሊት ፡ ሁልጊዜ ፡ የሚያከብሩት
ዘለዓለማዊ ፡ ንጉሥ ፡ ኃያል ፡ የክብር ፡ ጌታ
መጽሐፉን ፡ የከፈተ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ

አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ
ውዳሴና ፡ ዕልልታ
አምልኮና ፡ ስግደት
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)

የወደቁ ፡ መላዕክት ፡ አጋንንት ፡ በጥልቅ ፡ ያሉ
ስሙ ፡ ሲጠራባቸው ፡ ሁሌ ፡ ይንቀጠቀጣሉ
ተራሮች ፡ ሚጤሱለት ፡ ኮረብቶች ፡ ሚዘሉለት
ጌታ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የጽዮኑ ፡ ዓለም

አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ
ውዳሴና ፡ ዕልልታ
አምልኮና ፡ ስግደት
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)

በፍጥረት ፡ መጀመሪያ ፡ ከሙታንም ፡ በኩር
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ የሆነ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃለ ፡ እግዚአብሔር
ፀጋ ፡ እውነትን ፡ ተሞልቶ ፡ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያደረ
ክርስቶስ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ያለና ፡ የነበረ

አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ
ውዳሴና ፡ ዕልልታ
አምልኮና ፡ ስግደት
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)

ከዘር ፡ ከነገድ ፡ ሁሉ ፡ ከአገር ፡ ከወገን
እኛን ፡ በደሙ ፡ አጭቶ ፡ ካህናት ፡ ያደረገን
መንፈሱን ፡ ያፈሰሰ ፡ ፀጋውን ፡ የሰጠን
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን

አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ
ውዳሴና ፡ ዕልልታ
አምልኮና ፡ ስግደት
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)