ካከበርነው ፡ ያከብረናል (Kakebernew Yakebrenal) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg

፲ ፩
(11)

በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልፍ
(Bedebebeqosh Qenu Endayalf)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 8:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

እምነት ፡ ሲለካ ፡ በሰፈር ፡ ጓዳ ፡ ሲፈተሽ ፡ በችግር (አሃሃ)
ዐይኖች ፡ በእምባ ፡ ሲሞሉ ፡ ኃያል ፡ ጉልበቶች ፡ ሲላሉ (ኦሆሆ)
የሠማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስንጠፋ ፡ አይገድህም ፡ ወይ (አሃሃ)
ማለት ፡ አልቀረም ፡ ይሆናል ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ ደርሶ ፡ አድኖናል (ኦሆሆ)
ከእግሩ ፡ ስር ፡ ዝቅ ፡ ብለን ፡ ልናከብረው ፡ ይገባናል (አሃሃ)

አዝ፦ የገባው ፡ ሲያመሰግን ፡ ያልገባው ፡ ሲያጉረመርም
ስህተት ፡ ፈላጊዎች ፡ ሲያሙ ፡ እየተራወጡ ፡ ሲሻሙ (ኦሆሆ)
መገለጥ ፡ ከላይ ፡ ሲለቀቅ ፡ ዲያቢሎስ ፡ በታች ፡ ሲጨነቅ (እህህ)
ዳዊቶች ፡ ሲፈነጥዙ ፡ ሚልኮሎች ፡ ደግሞ ፡ ሲያፌዙ (ኦሆሆ)
ሁሉም ፡ ስራውን ፡ ይሰራል ፡ ነበር ፡ አለ ፡ ይኖራል (አሃሃ)
እኔም ፡ ስራዬን ፡ እሰራለው ፡ ለአምላኬ ፡ እዘምራለሁ (አሃሃ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (አሃሃ)

የዓለም ፡ ሙገሳን ፡ ነቀፋን ፡ በመስማት ፡ ጊዜን ፡ አናጥፋ (አሃሃ)
ተረት ፡ ጨዋታ ፡ ይቅርብን ፡ አስቸኳይ ፡ ስራ ፡ አለብን (አሃሃ)
መመሪያው ፡ በእኛ ፡ ከሰራ ፡ አይደርስብንም ፡ ኪሳራ ፡ (አሃሃ)
ነገር ፡ ሚስጥሩ ፡ ደርሶናል ፡ ካከበርነው ፡ ያከብረናል ፡ (አሃሃ)
ምሥጋና ፡ ስንሰዋለት ፡ ማዳኑንም ፡ ያሳየናል (አሃሃ)

አዝ፦ የገባው ፡ ሲያመሰግን ፡ ያልገባው ፡ ሲያጉረመርም
ስህተት ፡ ፈላጊዎች ፡ ሲያሙ ፡ እየተራወጡ ፡ ሲሻሙ (ኦሆሆ)
መገለጥ ፡ ከላይ ፡ ሲለቀቅ ፡ ዲያቢሎስ ፡ በታች ፡ ሲጨነቅ (እህህ)
ዳዊቶች ፡ ሲፈነጥዙ ፡ ሚልኮሎች ፡ ደግሞ ፡ ሲያፌዙ (ኦሆሆ)
ሁሉም ፡ ስራውን ፡ ይሰራል ፡ ነበር ፡ አለ ፡ ይኖራል (አሃሃ)
እኔም ፡ ስራዬን ፡ እሰራለው ፡ ለአምላኬ ፡ እዘምራለሁ (አሃሃ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (አሃሃ)

መንፈስ ፡ ዘወትር ፡ ዝግጁ ፡ ነው ፡ ሥጋም ፡ እንደሆነ ፡ ደካማ ፡ ነው ፡ አሃሃ
ፊት ፡ ካሳዩት ፡ ካዘኑለት ፡ አይመቸው ፡ አይሞላለት ፡ ኤሄሄ
እንዳይገፋን ፡ በትዕቢቱ ፡ መጐሸም ፡ ነው ፡ መድሃኒቱ ፡ አሃሃ
ጉድለት ፡ ብቻ ፡ እየቆጠርን ፡ ማጉረምረሙን ፡ እንተውና (አሃሃ)
ቀና ፡ እንበል ፡ ጌታን ፡ እንይ ፡ በምሥጋና ፡ ድል ፡ አለና (አሃሆ)

አዝ፦ የገባው ፡ ሲያመሰግን ፡ ያልገባው ፡ ሲያጉረመርም
ስህተት ፡ ፈላጊዎች ፡ ሲያሙ ፡ እየተራወጡ ፡ ሲሻሙ (ኦሆሆ)
መገለጥ ፡ ከላይ ፡ ሲለቀቅ ፡ ዲያቢሎስ ፡ በታች ፡ ሲጨነቅ (እህህ)
ዳዊቶች ፡ ሲፈነጥዙ ፡ ሚልኮሎች ፡ ደግሞ ፡ ሲያፌዙ (ኦሆሆ)
ሁሉም ፡ ስራውን ፡ ይሰራል ፡ ነበር ፡ አለ ፡ ይኖራል (አሃሃ)
እኔም ፡ ስራዬን ፡ እሰራለው ፡ ለአምላኬ ፡ እዘምራለሁ (አሃሃ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (አሃሃ)

ሳይጀምረኝ ፡ ልጀምረው ፡ ዛሬን ፡ ከሰጠኝ ፡ ልኑረው (አሃሃ)
በማለዳ ፡ ልነሳና ፡ ድምጼን ፡ ላውጣ ፡ በምሥጋና (አሃሃ)
ወፎች ፡ ለምን ፡ ይቅደሙኝ ፡ ላሰማቸው ፡ ሳያሰሙኝ (አሃሃ)
ቀኑን ፡ ልቀድስ ፡ ለጌታ ፡ በዝማሬ ፡ አፌን ፡ ልፍታ (አሃሃ)
የመምጫውን ፡ ቀን ፡ ማን ፡ ያውቃል ፡ ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ማራናታ