From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ
ትሻለኛለህ ፡ አባባ
ሊያጠግብ ፡ ኩርማን ፡ እንጀራ
ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ብሰራ
አለቀ ፡ ኃይሌ ፡ ጉልበቴ
በክንድህ ፡ ጥቂት ፡ ዘመኔ
በአንተ ፡ ቤት ፡ ልረፍ ፡ መድህኔ (፪x)
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ
ትሻለኛለህ ፡ አባባ
ከዛሬ ፡ ነገ ፡ ይሻል ፡ ብዬ
ብዙ ፡ ሮጥኩኝ ፡ ጨርቄን ፡ ጥዬ
በዓለም ፡ ያየሁት ፡ አበሳ
እስከመቼም ፡ አይረሳ
ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ሩጫዬ
መስቀልህ ፡ ሆኗል ፡ ምርጫዬ (፪x)
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ
ትሻለኛለህ ፡ አባባ
ክፉ ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ የጐደላት
ጦር ፡ እንጂ ፡ ሰላም ፡ የሌላት
ሰው ፡ በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሮ
ወደ ፡ አውሬነት ፡ ተቀይሮ
እርስ ፡ በርስ ፡ ስታብላላ
በውሸት ፡ ዕውቀት ፡ አታላ (፪x)
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ
ትሻለኛለህ ፡ አባባ
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጌታ ፡ ከመሆን
ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ከመግዛት
እራስን ፡ ላንተ ፡ አስገዝቶ
ድሃ ፡ ተብሎ ፡ መጠራት
ክብር ፡ እንደሆነ ፡ አወቅሁ ፡ ጠንቅቄ (፪x)
በቤትህ ፡ ልኑር ፡ ማቅቄ
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ
ትሻለኛለህ ፡ አባባ
|