ሰላም ፡ ሰላም ፡ ሰላም (Selam Selam Selam) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Akiel Dama)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ሰላም ሰላም ሰላም ሰላም
ሰላም ሰላም ሰላም ሰላም ለአለም
ለአለም ያለ ኢየሱስ የለም

1. ሁሉም በየቤቱ ሰይፉን እየሳለ
አደባባይ ወጥቶ ሰላም ሰላም ካለ
ሰው እራሱን እንጂ ማንን ያታልላል
ይልቅ እግዚአብሄርን ቢማፀን ይሻላል

ሰላም ...

2. ምድርን በደም ሊያጥብ ዲያብሎስ ተነስቷል
ያሳብባል እንጂ ሰው መች ተረድቷል
ሞትና ጭንገፋ ከምድር እንዲያበቃ
የአዳም ዘር ይታረቅ ከሰላም አለቃ

ሰላም ...

3. ከዘለአለም ሞት ሰውን ሁሉ ሊያድን
ከሰማይ ሰማያት የወረደውን መድኅን
አልቀበል ብሎ ሰው እየተጋፋ
ምን ያስደንቀዋል ደህንነት ቢጠፋ

 ሰላም ...