ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ (Nefsie Hoy Egziabhieren Barki) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Akiel Dama)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ነፍሴ ሆይ እግዚአብሄርን ባርኪ አጥንቶቼም ታላቅ ስሙን ባርኩ
ጠላት ቢደነፋም አያልፍም ከልኩ
ነፍሴም አጥንቴም እግዚአብሄርን ባርኩ

1 ጮራ ሲፈነጥቅ ኦሆ ጎህ ሲቀድ ማለዳ አሃ
ገልጠን እናያለን የጠላትን ጓዳ
ሜዳውን የሞላው ኦሆ የአራዊት መንጋ አሃ
ከጫካው ይገባል ይህ ለሊት ሲነጋ
ማን ችሎት ይቆማል ጌታ ከተዋጋ

ነፍሴ ሆይ ...

2. ጀንበሯ ልትወጣ ደቂቃ ሲቀራት
አይን ቢወጉ አያሳይ የጨለማው ብርታት
ጌታም ዘንበል ሊል ደቂቃ ሲቀረው
የፈተናው አይነት ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነው
ቢሆንም ግድ የለም ድል የእግዚአብሔር ነው

ነፍሴ ሆይ ...

3. እግዚአብሔር አይቷል የእንባ ኑሮሽን
አመስግኚው ነፍሴ ተይው እሮሮሽን
አንቺ ስታለቅሺ ጠላት ይደሰታል
መውደቅሽን ሊያውጅ ከበሮ ይመታል
እልል በይ ነፍሴ ፈራጅሽ ተነስቷል

ነፍሴ ሆይ ...

4. ከሰማይ የራቀ ከምድር የጠለቀ
ሰው ማቅረብ ይችላል ማመስገን ካወቀ
እግዚአብሔር ሲከብር ዲያብሎስ ይወድቃል
ተራራው ይናዳል ውቅያኖስ ይደርቃል
የአመስጋኞች ክንድ ጠላትን ያደቃል

ነፍሴ ሆይ ...

5. ጀንበሯ ልትወጣ ደቂቃ ሲቀራት
አይን ቢወጉ አያሳይ የጨለማው ብርታት
ጌታም ዘንበል ሊል ደቂቃ ሲቀረው
የፈተናው አይነት ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነው
ቢሆንም ግድ የለም ድል ጌታ አሸናፊ ነው