ኢየሱስ ጌታ ነው (Eyesus Geta New) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አልበም
(Tamrat 5)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ኢየሱስ ጌታ ነው (አዝማች)

አይቸኩልም ጌታ አርፍዶ ይነሳል
ግን ማንም አይቀድመው በጊዜ ይደርሳል 
ጌታን ከዙፋኑ ለማውረድ የለፉ
ትላንት የነበሩ ዛሬ ግን የጠፉ 
እጅግ ብዙ ብዙ ናቸው
ታዲያ ምን ያደርጋል ሞት አሸነፋቸው

በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው
ትላንትናም ዛሬም  ለዘለአለም ህያው ነው

መቃብር ጠባቂው በከንቱ ሲጉላላ
ኢየሱስ ተነስቶ ከተማውን ሞላ
ዛሬም ባዶ ህንፃ ሰይጣን ያስጠብቃል
ጌታ በየጏዳው ህዝቡን ያነቃቃል
ግሩም ነው ድንቅ ነው 
ዛሬም ለዘለአለም ኢየሱስ ጌታ ነው

በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው
ትላንትናም ዛሬም  ለዘለአለም ህያው ነው

ነቢያት ነን ባዮች በስሙ የነገዱ
የአምልኮ መልክ ይዘው ሃይሉን ግን የካዱ
ስተው እያስቱ ጥቂት ዘመን ኖሩ
ቀናቸው አበቃ ሞቱ ተቀበሩ
አለ በአፈር አጥንታቸው
በጎልጎታ ያለው ባዶ መቃብር ነው

በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው
ትላንትናም ዛሬም  ለዘለአለም ህያው ነው

እውነት መሰል ተረት ይዘው የተነሱ
በወሬ መሰላል ሰማይ የደረሱ
ፈጣሪ አማልክት መባል ያማራቸው
ከኑፋቄያቸው ጋር ምድር ዋጠቻቸው
ተረታቸው ወዴት አለ
እውነተኛው አምላክ ኢየሱስ ነው ተብለ

በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው
ትላንትናም ዛሬም  ለዘለአለም ህያው ነው