እንግባ ፡ ንስሃ (Enegba Neseha) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Akiel Dama)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

1. ምድራችን ከጥንቱ የክርስቲያን ደሴት ስትባል ኖራለች
እዉነቱ ግን ሲታይ የእልቂት የጦርነት አውድማ ሆናለች
ሽማግሌ ወጣት ወንድ ሴት ሳይባል እንፁም ውኅ
ሁላችንም ወድቀን እንግባ ንሰኅ

ጌታ ሆይ ትረዳናለህ ወይ
አዎ ካልከን ከረዳሀን የፍቅር ሰው አድርገን

2. በየአደባባዩ መምህርና ጌታ መባል እንወዳለን
በፀሎት ርዝመት እያመካኘን ሰውን እንገፋለን
ላይ ላያችን ሲታይ ያለን እንመስላለን የመላዕክት ዝርያ
ውስጣችን ተሞልቶ በቅሚያ በዝርፊያ

ጌታ ሆይ ትረዳናለህ ወይ
አዎ ካልከን ከረዳሀን እውነተኞች አድርገን

3. ስልጣን ማን ሰጥቶናል አንዱን ለመቀበል ሌላውን ለማባረር
ማን ፈራጅ አድርጎናል ማን አስቀምጦናል በነሙሴ ወንበር
ይልቅ እንደኢየሱስ ዝቅ እንበልና እንጠብ እግር
እኛ እንዋረድ እግዚአብሔር ይክበር

ጌታ ሆይ ትረዳናለህ ወይ
አዎ ካልከን ከረዳሀን ትሁታን አድርገን

4. እስከዛሬ ድረስ እየተናገርን ብዙ ዘመን ኖርን
ቃል አላነሰንም ከእንግዲህ በላ ኑሮ ነው የቀረን
የቃል ሰው አንሁን አንባቢ አስነባቢ ተግባር የጎደለው
ብንጠይቅ ሊሰጠን ኢየሱስ ሙሉ ነው

ጌታ ሆይ ትረዳናለህ ወይ
አዎ ካልከን ከረዳሀን እውነተኞች አድርገን

5. ምድራችን ከጥንቱ የክርስቲያን ደሴት ስትባል ኖራለች
እዉነቱ ግን ሲታይ የእልቂት የጦርነት አውድማ ሆናለች
ሽማግሌ ወጣት ወንድ ሴት ሳይባል እንፁም ውኅ
ሁላችንም ወድቀን እንግባ ንሰኅ

ጌታ ሆይ ትረዳናለህ ወይ
አዎ ካልከን ከረዳሀን የፍቅር ሰው አድርገን

6. በየአደባባዩ መምህርና ጌታ መባል እንወዳለን
በፀሎት ርዝመት እያመካኘን ሰውን እንገፋለን
ላይ ላያችን ሲታይ ያለን እንመስላለን የመላዕክት ዝርያ
ውስጣችን ተሞልቶ በቅሚያ በዝርፊያ