እግዚአብሔር ፡ ሆኖኛል ፡ መተማመኛ (Egziabhier Honognal Metemamegna) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Akiel Dama)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁ
እግዚአብሔር ሆኖኛል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ

1. ህይወት ረቂቅ ናት መች እንዲህ በወሬ
መረር ከረር ስትል ከትናንቱ ዛሬ
መንገዷ ረጅም ነው አይደረስባት
እጅግ ትመራለች ጌታ ከሌለባት
እኔ ግን ድኛለሁ ከኀጢአት ውጥንቅጥ
እኖራለሁ ኑሮ እጅግ የሚጣፍጥ
አይቆረቁረኝም መኝታዬ
ይመስገን ጌታዬ

በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁ
እግዚአብሔር ሆኖኛል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ

2. እይኔ ተከፈተ አምላኩን ያወቀ
አንዴም አልተረታ አንዴም አልወደቀ
የአለም ማባበል የሰይጣንን ደባ
ተዋግቶ አሸንፎ ድል አድርጎ ገባ
ወዲያ ወዲህ መሮጥ ስጋን ተከትሎ
በሽተኛ መሆን ህይወትን አቁስሎ
በእውነተኛ ልብ ከጠራነው
ኢየሱስ መልስ ነው

በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁ
እግዚአብሔር ሆኖኛል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ

3. በኢየሱስ እጅ ነው ትርጉም ያለ ህይወት
ታዲያ ምን ያደርጋል ሰው አላወቀበት
በመውጣት በመውረድ ነፍሱን ያባክናል
ላያጠግብ እንጀራ ገንዘብ ይመዝናል
እኔ ግን አንድ ቀን ብርሃን በርቶልኛል
የምድር ድንኳኔን ጌታ አሙቆልኛል
ደግሞም በሚመጣው አዲስ አለም እኖራለሁ ዘላለም

በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁ
እግዚአብሔር ሆኖኛል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ

4. እዚህ ደርሻለሁ ዘመናት አልፌ
ለይቼ አውቄያለሁ ጉዳትና ትርፌን
ከእንግዲህ በኃላ የቀረኝ ዘመኔ
ጉያው ገብቻለሁ እርሱ ነው ተገኔ
ሰውም አያድንም ብርም አያድንም
ክብርም አያድንም እውቀት አያድንም
ሰው ጌታን ከያዘ ግን ምን ይሆናል
በኢየሱስ ይድናል

በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁ
እግዚአብሔር ሆኖኛል መተማመኛ
ከጥፋት ሁሉ መዳኛ