From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ጌታ ፡ ምስኪኖችን ፡ ይወዳል
ጐስቋሎችን ፡ ይወዳል
ሰው ፡ የጣለውን ፡ ያነሳል
የተረሳውን ፡ ያስታውሳል
ዓይኖቹ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ያያሉ
ለዓይነስውራን ፡ መሪ ፡ ነው
ለአካለ ፡ ስንኩል ፡ ድጋፍ ፡ ነው
ለረሃብተኞች ፡ መጋቢ
ወላጅ ፡ አልባውን ፡ ሰብሳቢ
ለደሃ ፡ አደጐች ፡ አባት ፡ ነው
ለመበለቶች ፡ ዳኛ ፡ ነው
ሃዘንተኛውን ፡ ያጽናናል
ጌታ ፡ ለሁሉም ፡ ይሆናል
ጌታ ፡ ሰርግ ፡ ቤት ፡ ይገኛል
ውሃውን ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ያደርጋል
በለቅሶም ፡ በሀዘን ፡ ቦታ
ተገኝቶ ፡ ያጽናናል ፡ ጌታ
ህመመተኛውን ፡ ደጋፊ
አስታማሚ ፡ አልጋ ፡ አንጣፊ
ሐኪም ፡ ነው ፡ በሽታን ፡ ያውቃል
ፈዋሽ ፡ ነው ፡ ነጻ ፡ ያወጣል
ካህን ፡ ነው ፡ ሕዝብን ፡ ይመራል
ንጉሥ ፡ ነው ፡ ያስተዳድራል
ወታደር ፡ ነው ፡ አገር ፡ ጠባቂ
ከአውሬ ፡ ከአንበሳ ፡ ነጣቂ
አገር ፡ ሲወረር ፡ በግፍ
ሕዝብ ፡ እንደ ፡ ቅጠል ፡ ሲርግፍ
ከምስኪኖች ፡ ጐን ፡ ይቆማል
መርከቡን ፡ በባሕር ፡ ያሰጥማል
ሃዘን ፡ ትጥቅህን ፡ አይፍታ
ችግርክን ፡ ንገር ፡ ለጌታ
አያልፍም ፡ ከንፈሩን ፡ መጥጦ
ያነሳል ፡ እጅን ፡ ጨብጦ
|