አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው (Anten Metebeq Bezu Terf Alew) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አኬል ፡ ዳማ
(Tamrat 5)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲያኛው ፡ አለም

አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ባዶ ፡ የቀረ
መከራ ፡ ገጥሞት ፡ የተማረረ
አላየሁኝም ፡ አልሰማሁኝም
ያለፈው ፡ ዘመን ፡ ታሪክ ፡ ይመርመር ፡ ከቶ ፡ አይገኝም

አዝ ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲያኛው ፡ አለም

ሥጋ ፡ ለባሹን ፡ የተደገፈ
በሰው ፡ ስራ ፡ ላይ ፡ አይኑ ፡ ያረፈ
ምርኩዙ ፡ ሲወድቅ ፡ እሱም ፡ ወደቀ
አንተን ፡ ያለው ፡ ግን ፡ የማታ ፡ ማታ ፡ ደስ ፡ ብሎት ፡ ሳቀ

አዝ ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲያኛው ፡ አለም

እኔም ፡ ባለፈው ፡ ሰውን ፡ አይቼ
ተጎድቻለሁ ፡ መንገዴን ፡ ስቼ
ከእንግዲህ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ
ዛሬ ፡ ባለቅስም ፡ የማታ ፡ ማታ ፡ እኔም ፡ ስቃለሁ

አዝ ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲያኛው ፡ አለም

የእምባዬ ፡ ፍሬ ፡ ለምልሞ ፡ ባላይ
ቢያጠወልገው ፡ የበጋው ፡ ፀሀይ
የመጨረሻው ፡ ዝናብ ፡ ይዘንባል
የእኔም ፡ ፈተና ፡ ከነኮተቱ ፡ ገደል ፡ ይገባል

አዝ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ