አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ (Abietu Gulbetie Hoy Ewedehalehu) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(5)

አልበም
(Tamrat 5)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ 4x (አዝማች)

አዝ

ጎልያድን መሳይ አስፈሪ ጀግና
ግዙፍ ሰውነት ግሩም ቁመና
ራሱን ተመቶ የተዘረረው
በኔ ሃል አይደል ባንተ ጉልበት ነው
ልላ ምን አለኝ ሃሌሉያ ነው

አዝ

ሳኦል በክፋት ጦሩን ሲሰብቅ
ከግድግዳ ጋር ነፍሴን ሊያጣብቅ
ቢወረውርም ደግሞ ደጋግሞ
ጋሻ ሆነልኝ ያንተ እጅ ቀድሞ
አቤት ማዳንህ ይግነን ዙፋንህ

አዝ

ከውስጥ ከውጭ ከቅርብም ከሩቅ
ተሰድጃለሁ ምክንያቱን ሳላውቅ
የምምለጫ አለት ምሽግ የሆንከኝ
አንተ ነህ ጌታ የሰበሰብከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ

አዝ

በጨለማ ውስጥ በሞትም ጥላ
በጥፋት ጉድጓድ በሌለው መላ
ባለቀ ሰዓት ደርሰህልኛል
የነሀሱን ደጃፍ ሰብርህልኛል
ታላቅ ነው ሀይልህ ከፍ ይበል ስምህ