ዘንበል ፡ ይላል ፡ ጌታ (Zenbel Yelal Gieta) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝማች
በእምነት ይኖራል ጻዲቅ ጻዲቅ በእምነት ይኖራል/2
ቢያፈገፍግ ወደ ኋላ
በእኔ ዘንድ ይሆናል የተጠላ
በእርሱ ደስ አይላትም ነፍሴ
ብሏል ኢየሱሴ
በትዕግስት ጠብቀው በዝምታ
ዘንበል ይላል ጌታ

አትሞኝ ወገኔ ዘመኑ አልቋልና
ተጉዘህ ልትጨርስ ረጅሙን ጎዳና
ጥቂት ነው የቀረህ መለከት ልትሰማ
ገብተህ እፎይ ልትል በውቧ ከተማ

አዝ፦ በዘመን እላቂ በተዘጋ ደጁ
ምን ያለው ሞኝ ነው ለዓለም ሚሰጥ እጁን ለዓለም ሚሰጥ እጁን
ተጉዞ ተጉዞ ሩብ ሰዓት ሲቀረው
እንዲያፈገፍግ ማነው የመከረው ማነው የመከረው

አዝ፦ የመንግሥቱ ካህን ልትሆን መርጦሃል
በሰማዩ ስፍራ ጌታ አስቀምጦሃል ጌታ አስቀምጦሃል
ራስህን አታቅልል አትመኝ አቧራ
የከበረ ስም ነው ባንተ የተጠራ
አሜን ባንተ የተጠራ

አዝ፦ ዓለም ውሸቷን ብትል ቀና ደፋ
ወዝህ ያለቀ እለት አንቅራ ልትተፋ አንቅራ ልትተፋ
ከደጃፏ ቆመህ ኃጢአት አትቀላውጥ
በእግዚአብሔር ደጃፍ መጣልን ምረጥ መጣልን ምረጥ

አዝ፦ ተረሳሁኝ አትበል የሚረሳህ ማን ነው
ጌታ የቀረፀህ በእጁ መዳፍ ነው
አሜን በእጁ መዳፍ ነው
አልታየሁም አትበል አምላክህ ያይሃል
ታግሰህ ብትቆይ ዘምበል ይልልሃል አሜን ዘምበል ይልልሃል

አዝ