From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦
ታሪኬ ፡ የጀመረው
በቀራኒዮ ፡ ነው
በመስቀሉ ፡ ግርጌ
አጋጣሚ ፡ አይደለም
መወለድ ፡ ማደጌ
ሠይጣን ፡ ሲቀጠቀጥ
እራሱ ፡ ሲመታ
ባርነቴ ፡ ሲሻር
ሰንሰለት ፡ ሲፈታ
ጠላት ፡ ሲመሽበት ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሲነጋ
ይኼ ውብ ፡ ታሪኬ ፡ ተጀመረ ፡ እዚያጋ
ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ ለጌታዬ
ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በዜማዬ
ከወህኒ ፡ ከፍርድ
እኔኑ ፡ ሊያወጣ
ከድንግል ፡ ማርያም
ሥጋ ፡ ነስቶ ፡ መጣ
መልክ ፡ ውበቱን ፡ ተወ
የባርያን ፡ መልክ ፡ ያዘ
እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞትም
በፍቅር ፡ ታዘዘ
ከአደረገው ፡ በቀር ፡ ኢየሱሴ ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ የእራሴ
አዝ፦ ታሪኬ ፡ የጀመረው ፡ በቀራኒዮ ፡ ነው
በመስቀሉ ፡ ግርጌ ፡ በአጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ መወለድ ፡ ማደጌ
ሠይጣን ፡ ሲቀጠቀጥ ፡ እራሱ ፡ ሲመታ
ባርነቴ ፡ ሲሻር ፡ ሰንሰለት ፡ ሲፈታ
ጠላት ፡ ሲመሽበት ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሲነጋ
ይኼ ውብ ፡ ታሪኬ ፡ ተጀመረ ፡ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በዜማዬ
በቃሉ ፡ እውነተኛ
በተግባሩም ፡ ደግ
ከፋት ፡ የሌለበት
የእግዚአብሔር ፡ በግ
እኔን ፡ ሊያዘምረኝ ፡ እርሱ ፡ አለቀሰ
እኔን ፡ ሊያከብረኝ ፡ ውረደትን ፡ ለበሰ
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥም ፡ አለው
ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ለእርሱ ፡ ነው
አዝ፦ ታሪኬ ፡ የጀመረው ፡ በቀራኒዮ ፡ ነው
በመስቀሉ ፡ ግርጌ ፡ በአጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ መወለድ ፡ ማደጌ
ሠይጣን ፡ ሲቀጠቀጥ ፡ እራሱን ፡ ሲመታ
ባርነቴ ፡ ሲሻር ፡ ሰንሰለት ፡ ሲፈታ
ጠላት ፡ ሲመሽበት ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሲነጋ
ይኼ ውብ ፡ ታሪኬ ፡ ተጀመረ ፡ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በዜማዬ
ብዙ ፡ የነበረውን
እዳዬን ፡ ሻረልኝ
ኃጢአቴን ፡ በሁሉ ፡ ከኋላው ፡ ጣለልኝ
በመስቀል ፡ ጠርቆ
ከእኔ ፡ አስወግዶ
ጨካኙን ፡ ከሳሼን
ባዶ ፡ እጁን ፡ ሰደደው
እዛጋ ፡ ጀመረ ፡ ታሪኬ
ምሥጋና ፡ ይብዛለት ፡ አምላኬ
አዝ፦ ታሪኬ ፡ የጀመረው ፡ በቀራኒዮ ፡ ነው
በመስቀሉ ፡ ግርጌ ፡ በአጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ መወለድ ፡ ማደጌ
ሠይጣን ፡ ሲቀጠቀጥ ፡ እራሱን ፡ ሲመታ
ባርነቴ ፡ ሲሻር ፡ ሰንሰለት ፡ ሲፈታ
ጠላት ፡ ሲመሽበት ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሲነጋ
ይኼ ውብ ፡ ታሪኬ ፡ ተጀመረ ፡ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በዜማዬ (፪x)
|