ሶስት ፡ መንገድ ፡ የለም (Sost Menged Yelem) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

፡ ፡ ያዝ ፡ ለቀቅ ፡ ሔድ ፡ መጣ ፡ ገባ ፡ ወጣ
ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ሲያጣ
ወይ ፡ ከየሱስ ፡ ወይ ፡ ከዓለም ፡ ምረጥ ፡ እንጂ
ሦስት ፡ መንገድ ፡ የለም

እንጀራ ፡ ለመብላት ፡ ሺ ፡ ተሰበሰበ
መስቀል ፡ ለመሸከም ፡ አንድም ፡ አልቀረበ
ተዓምር ፡ ለማየት ፡ እልፍ ፡ ሰው ፡ ቢንጋጋ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው፡ ፡ በጦር ፡ የተወጋ

 ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ

በየመንገድ ፡ ወራጅ ፡ ሞልቷል ፡ ተሳፋሪ
ከጠጣ ፡ በኋላ ፡ ወጭቱን ፡ ሰባሪ
ትላንትን ፡ አትርሳ ፡ አትሁን ፡ ውለታ ፡ ቢስ
ገባ ፡ ወጣ ፡ አትበል ፡ ጸንተህ ፡ ቁም ፡ በየሱስ

 ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ

ድንኳን ፡ አስከሚወርድ ፡ ድግስ ፡ ተጠናቆ
ስደት ፡ አስኪመጣ ፡ ነጻው ፡ ዘመን ፡ አልቆ
ስንት ፡ ሰው ፡ ዘምሯል ፡ ስንቱስ ፡ አጨብጭቧል
በመከራው ፡ ቀን ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ብዙዎችን ፡ ታዝቧል

 ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ

እራሱን ፡ ላይገዛ ፡ ላይችል ፡ መታዘዙን
በሞቅታ ፡ ጊዜ ፡ ቃል ፡ ኪዳነ ፡ ብዙ
ሆኖለት ፡ ላይከፋል ፡ ስለት ፡ የተሳለ
አሁን ፡ በዚህ ፡ መሃል ፡ ባለዳ ፡ ስንት ፡ አለ?

 ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ

መና ፡ ካዘነበ ፡ ከምንጩ ፡ ካጠጣን
ከአመድ ፡ አንስቶን ፡ ከረግረግ ፡ ካወጣን
ካበላን ፡ ካጠጣን ፡ ካከበረን ፡ ኋላ
መስቀሉን ፡ አንሽሽ ፡ አብረን ፡ እንጉላላ

 ፡ ፡ :አዝ፦ ያዝ ፡ ለቀቅ