ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (Selam Eyesus New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)

ለነገድ ፡ ለጐሳ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በአገሮች ፡ መሃል ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለሰባቱ ፡ አህጉራት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለዓለም ፡ በሙሉ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ከሰው ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ሥጋ ፡ ከለበሰ
ባንዱ ፡ ስናማርር ፡ ይመጣል ፡ የባሰ
ይኸኛው ፡ ሲያጠራ ፡ ያኛው ፡ ሲያደፈርስ
ባለንበት ፡ መሔድ ፡ ውኃ ፡ ቅዳ ፡ መልስ

አንዴ ፡ ከጠጣን ፡ እንዳንጠማ
የችግር ፡ ወሬ ፡ እንዳንሰማ
ማረፍ ፡ ከፈለግን ፡ እስክወዲያኛው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ዳኛው

አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)

በቤተስብ ፡ መሃል ፡ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለባለትድሮች ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለወንድም ፡ ለሴትም ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ለያንዳንዱ ፡ ሕይወት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ሠይጣን ፡ ጥላውን ፡ ሲጥል ፡ ገብቶ ፡ ሲያምታታ
ቤተሰብ ፡ ሲበትን ፡ ትዳርን ፡ ሲፈታ
ቤቶች ፡ ፈረሱና ፡ ተዘጉና ፡ ደጆች
ጐዳናውን ፡ ሞሉት ፡ የመንገድ ፡ ዳር ፡ ልጆች

ምስቅልቅል ፡ ላለ ፡ ሕብረተሰብ
ሩቅ ፡ አያስኬድም ፡ መፍትሔው ፡ ቅርብ
የጌታን ፡ መንግሥት ፡ ጽድቁን ፡ ብትሹ
አሁን ፡ ይፈታል ፡ ዕንቆቅልሹ

አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)

ማታ ፡ ስንተኛ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ጥዋት ፡ ስንነሣ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በመንገድ ፡ ስንሔድ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በሥራ ፡ በዕረፍት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

እስቲ ፡ ዕራስህን ፡ ባትደልል ፡ ምን ፡ አለ
ጢርነቱ ፡ እንደሆን ፡ በልብህ ፡ ውስጥ ፡ አለ
ሲጋራ ፡ ብታጨስ ፡ ጫትም ፡ ብትበላ
ውስኪ ፡ ብትጠጣ ፡ አረቂና ፡ ጠላ

መተንፈሻ ፡ ነው ፡ አፍንጫ ፡ አይደል ፡ ጭስ ፡ ማውጫ
ሳንባ ፡ ሲቃጠል ፡ አንጀት ፡ ሲንጫጫ
አበላሽቶታል ፡ ወዝብ ፡ ጠረንህ
የሚያሳምር ፡ ኢየሱስ ፡ አለልህ

አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)