Tamrat Haile/Ahunem Alehu Bemerkebu/Sedom Gemora

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ

ሰዶም ገሞራ (፬x)

ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ

ግርግር ነው ከተማው አንዱ ሌላውን አይሰማው ሁሉም ይሮጣል ለንግዱ ጐዳናው ጠቧል መንገዱ ለነፍሱ አያስብ ለሰማይ ቤቱ ለዛሬ ብቻ ለለት ለለቱ

አዝ ሰዶም ገሞራ (፬x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ

ወንድ ከወንድ ጋብቻ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ በፍትወት እሳት ሲቃጠል ሲጋደም በየስርቻ እንሰሳ ሆነ ይሄ ክቡር ሰው መድኋኒት የለሽ ደዌ ጨረሰውድ

አዝ ሰዶም ገሞራ (፬x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ

ሕጻን አይሉ አዋቂ አንዱ በሌላው ሸማቂ ቀድሞ ጣዩ አልታወቀ እንጂ ሰው ሁሉ ጨብጧል ፈንጂ የፍቅር ኑሮ የዕርቅ ሰላም ክፋት ጠረገው ጠፋ ካለም

አዝ ሰዶም ገሞራ (፬x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ

ልጅ የናቱን ሆድ ረገጠ አባትም ልጁን ገላመጠ እናትም ጣለች ልጇን ቀረቀረችው ደጇን ጣራው ዘበጠ ቤቱ ተናጋ ዳኛ ጠፋና የሚያረጋጋ

አዝ ሰዶም ገሞራ (፬x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ