ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር (Keber Keber Keber) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር
ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ በሰማይ ፡ በምድር

መካኒቱን ፡ በልጅ ፡ የባረካት
ደስ ፡ የተሰኘች ፡ ሴት ፡ ያደረካት
ምስኪኑን ፡ ከአመድ ፡ ያነሳኸው
ለሹመት ፡ ሽልማት ፡ ያበቃኸው

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር

ባሕሩን ፡ ለሁለት ፡ የከፈልከው
ሾላውን ፡ ከስሩ ፡ የነቀልከው
ለደካማው ፡ ኃይልን ፡ የሰጠኸው
በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ያራመድከው

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር

ዘንዶውን ፡ የወጋህ ፡ የቆራረጥክ
ጠንካራውን ፡ አለት ፡ የሰነጠክ
የተራበችውን ፡ ነፍስ ፡ ያጠገብክ
የተበተኑትን ፡ የሰበስብክ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር

የእስረኞችን ፡ ጩኸት ፡ አዳምጠሃል
የወህኒውን ፡ መዝጊያ ፡ ሰባብረሃል
ሰው ፡ የረሳቸውን ፡ አስታውሰሃል
ያልጋ ፡ ቁራኞችን ፡ ፈውሰሃል
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር