ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ (Gieta Hoy Atmetam Hoy) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በእሳት ፡ ቁጥቋጦ ፡ የተገለጥከው
የአብርሃም ፡ የይስሐቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ነኝ ፡ ያልከው
መርዛሙን ፡ እባብ ፡ በትር ፡ ያደረክ
በመስኪን ፡ ነገር ፡ ባሕሩን ፡ የከፈልክ
መርዙን ፡ አውጣልን ፡ ከበትራችን
መድሃኒት ፡ አርገን ፡ ለምድራችን

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ

ጽድቅን ፡ ያደረግን ፡ እየመሰለን
ባዶ ፡ ቅንአት ፡ እያቃጠለን
የሕሊናን ፡ ድምጽ ፡ ተግሳጽን ፡ ንቆ
እግራችን ፡ ሲሮጥ ፡ ወደ ፡ ደማስቆ
በጽድቅ ፡ ጸሐይ ፡ ተገለጠልን
የእይናችንን ፡ ቅርፊት ፡ ጣልልን

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ

ፍቅራችን ፡ ያንገት ፡ የለበጣ ፡ ነው
ከአንተ ፡ አይደለም ፡ ከየት ፡ አመጣነው
አንዱን ፡ ከሌላው ፡ እንለያለን
ልብን ፡ አይደለም ፡ ልብስ ፡ እናያለን
ልባችን ፡ ጨካኝ ፡ ለሰው ፡ አይራራ
ዳስልንና ፡ ዓይናችን ፡ ይብራ

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ

የዕምነት ፡ አባቶች ፡ የቀደሙቱ
ለፍቅር ፡ ኖረው ፡ ለፍቅር ፡ ሞቱ
ታሪክ ፡ አንባቢ ፡ ሆነን ፡ ቀርተናል
ከአንተ ፡ በስተቀ ፡ ማን ፡ ይችለናል
የነሱ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነህ
እባክህ ፡ ጐብኘን ፡ ለስምህ ፡ ብለህ

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ

እሳትህ ፡ ቢነድ ፡ እንነጥራለን
መዶሻ ፡ ብትልክ ፡ እንሰባበራለን
ውኃ ፡ ብታፈስ ፡ እንጸዳለን
ዝም ፡ ካልከን ፡ ግን ፡ እንጐዳለን
ዛሬም ፡ ወዳንተ ፡ መጥተናልና
ቤትህን ፡ ሙላ ፡ በክብር ፡ ዳመና

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ