አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ (Ahunem Alehu Bemerkebu) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ተሳፍሬአለሁ ፡ በባቡሩ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከሰፈሩ
መቆም ፡ አልሻም ፡ በመንገዱ
ይቆራርጣል ፡ ሐዲዱ

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ስንቶች ፡ ተጓዙ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ወርደው ፡ ወጡ ፡ ተራራ
እየመሰለኝ ፡ ከጐኔ ፡ እያሉ
እኔ ፡ መች ፡ አወቅሁ ፡ እንደተበሉ

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ሳይመርምሩ ፡ ጊዜ ፡ ዘመኑን
ሳያውቁት ፡ ውኋው ፡ ጥልቅ ፡ መሆኑን
መንሸራሸር ፡ እያማራቸው
ሳያውቁት ፡ ድንገት ፡ ውጦ ፡ አስቀራቸው

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ስንቱን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
በፀጋው ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ በራሴ
ጌታ ፡ ሰጥቶኛል ፡ አቅሜን ፡ መለኪያ
ከፀጋው ፡ በቀር ፡ ያለኝ ፡ መመኪያ

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

መርከቡ ፡ ሲቆም ፡ በየወደቡ
ወራጁን ፡ ሲያወርድ ፡ ሌሎች ፡ ሲገቡ
በየከተማው ፡ ባቡሩም ፡ ሲያልፍ
እንዱን ፡ ሲያሳፍር ፡ ሌላውን ፡ ሲያራግፍ
ከጫፍ ፡ የሚደርስ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ እንጃ
አጽናኝ ፡ እያልኩኝ ፡ ይዣለሁ ፡ ምልጃ

አዝ፦ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ