መጣሁኝ (Metahugn) - ታጋይ ፡ ወልደማርያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

engda ngn

ታጋይ ፡ ወልደማርያም
(Tagay Woldemariam)
ዓ.ም. (Year): 2015
ርዝመት (Len.): 6:10
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የታጋይ ፡ ወልደማርያም ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Tagay Woldemariam)

ይኸው ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ
ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ
ይኸው ፡ ዙፋንህ ፡ ስር ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ
ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ

አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፫x)
የማመልክህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ምስክር ነኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ልከተልህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
የጠራኸኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)

ከጫፍ ፡ እስከ ፡ ጫፍ
ከአጥናፍ ፡ እስከ ፡ አጥናፍ
አምላክ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ሁሉ ፡ ይሰለፍ
ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነው

የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ተንበረከከ ፡ ይህንን ፡ አውቆ
ክብር ፡ ሚጋራ ፡ ደባሉን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርቆ
የእድሜዬም ፡ አፍላ ፡ ሽምግልናዬም ፡ ለእርሱ ፡ ይገዛል
ወዶ ፡ እና ፡ ፈቅዶ ፡ መላው ፡ እኔነቴ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል (፪x)

ይኸው ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ
ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ
ይኸው ፡ ዙፋንህ ፡ ስር ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ
ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ

አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፫x)
የማመልክህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ምስክር ነኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ልከተልህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
የጠራኸኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)

የእድሜው ፡ ልኩ ፡ ከእስከ ፡ የለው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ እየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ጠቢብ ፡ አዋቂው ፡ ቢሰበሰብም
በዚህች ፡ አይምሮው ፡ እርሱ ፡ አይለካም

የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ተንበረከከ ፡ ይህንን ፡ አውቆ
ክብር ፡ ሚጋራ ፡ ደባሉን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርቆ
የእድሜዬም ፡ አፍላ ፡ ሽምግልናዬም ፡ ለእርሱ ፡ ይገዛል
ወዶ ፡ እና ፡ ፈቅዶ ፡ መላው ፡ እኔነቴ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል (፪x)