ኢየሱስ (Eyesus) - ታጋይ ፡ ወልደማርያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታጋይ ፡ ወልደማርያም
(Tagay Woldemariam)

Tagay Woldemariam 3.jpg


(3)

አንግዳ ፡ ነኝ
(Engeda Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታጋይ ፡ ወልደማርያም ፡ አልበሞች
(Albums by Tagay Woldemariam)

ብዙ ፡ ማስጨነቅ ፡ በብዙ ፡ ማሸበር
ዙሪያዬን ፡ ሲዞሩ (፫x)
በአንድ ፡ መንገድ ፡ መጥቶ ፡ በታናቸው
አየሁ ፡ በሰባት ፡ መንገድ (፫x)
እጆቼኔም ፡ አልሰጥም ፡ ወጀቡን ፡ አይቼው
ማዕበሉን ፡ ፈርቼው (፪x)
ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ ካለው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው
ይበልጣል ፡ አምናለሁ (፫x)

ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ በጅግናው ፡ ጌታ
ፎክሮበታል ፡ እንደማይረታ
ሁሉም ፡ ቢናገር ፡ የስንፍና ፡ ቃል
ጐልያድ ፡ እንደድምቅ ፡ የማይቀር ፡ ነው

ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ በጅግናው ፡ ጌታ
ፎክሮበታል ፡ እንደማይረታ
ሁልም ፡ ቢናገር ፡ የስንፍና ፡ ቃል
ዮርዳኖስ ፡ እንደሚከፈል ፡ የማይቀር ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መመኪያ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ
ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት
ኢየሱስ ፡ ከጠላት ፡ ወጥመድ (፪x)

ፈርዖን ፡ ለምን ፡ ነው
መቸኮሉ ፡ ኃይሉን ፡ መጨረሱ (፫x)
በእግዚአብሔር ፡ ህዝብ ፡ ላይ
በትዕቢት ፡ ተነስቶ ፡ አንዲህ ፡ መገስገሱ
ለፍቶ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም
የሕዝቡ ፡ ጠባቂ ፡ የህዝቡ ፡ መከታ

ባህር ፡ ተከፈለ ፡ ሕዝቡም ፡ ተሻገረ
ፈርዖን ፡ ቀረ ፡ እዚያ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ኣምላክ ፡ ነው
ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ ስንቴ ፡ አምልጫለሁ
ጠላት ፡ ፊቴ ፡ መቆም ፡ አይችልም
የሚጠብቅኝ ፡ የሚተኛ ፡ አይደለም

ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መመኪያ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ
ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት
ኢየሱስ ፡ ከጠላት ፡ ወጥመድ (፪x)

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ ከላላ
ኢየሱስ ፡ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ ዓለት
ሆንከኝ ፡ ለእኔ ፡ አባት

ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ለራሱ ፡ የለየኝ ፡ ለክብሩ ፡ የቀባኝ
ተስፋ ፡ አስጨብጦኛል ፡ በመንገዴ ፡ ላይ ፡ ገብቶ
ለአፍታ ፡ አንደማይተወኝ
ድምጹን ፡ እየሰማሁ ፡ እከተለዋለሁ ፡ ከኋላው ፡ አሮጣለሁ
ወደ ፡ ታየለኝ ፡ ግብ ፡ አልቀርም ፡ እደርሳለሁ ፡ ዘልቄ ፡ እገባለሁ

ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው
መቼ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ቃሉ ፡ ሊሽረው
ወጥመዴን ፡ ስብሮ ፡ ያሻግረኛል
የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ ያወርሰኛል