From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ በአንተ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ አንተን ፡ ላመልክ ፡ ይገባኛል (፫x)
አዝ፦ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ በአንተ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ አንተን ፡ ላመልክ ፡ ይገባኛል (፫x)
አይ ፡ ይልኩትን ፡ ሁሉ ፡ አሳልፈኸኛል
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ተሸክመኸኛል
ውለታህን ፡ እያሰብኩ ፡ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ
ያደረክልኝን ፡ እንዴት ፡ እረሳለሁ
እንዴት ፡ እረሳለሁ (፬x)
ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
አምልኮም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ክብርም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ውዳሴም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ (፬x)
አዝ፦ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ በአንተ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ አንተን ፡ ላመልክ ፡ ይገባኛል (፫x)
አምላኬ ፡ ላከብርህ ፡ ብዙ ፡ ምክንያት ፡ አለኝ
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ለኔ ፡ የተደረገልኝ
ልጅህን ፡ በመስጠትህ ፡ ነፍሴን ፡ ታድገሃል
ሁልጊዜ ፡ እንዳመልክህ ፡ ነጻ ፡ አውጥተኸኛል
ነጻ ፡ አውጥተኸኛል (፬x)
ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
አምልኮም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ክብርም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ውዳሴም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ (፬x)
አዝ፦ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያላረከው ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ በአንተ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ አንተን ፡ ላመልክ ፡ ይገባኛል (፫x)
ጠላቴ ፡ እንዳሰበው ፡ አልተሳካለትም
ዛሬም ፡ በሕይወት ፡ አለሁኝ ፡ ከቶ ፡ አልጠፋሁም
ገና ፡ በአደባባይ ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ጌታን ፡ አመልክሃለሁ
ጌታ ፡ አመልካለሁ (፬x)
ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
አምልኮም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ክብርም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ውዳሴም ፡ ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
|