From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ጥዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ
የሽቶዬን ፡ ብልቃጥ ፡ በፊትህ ፡ አሰብራለሁ
አግርህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ አገዛልሃለሁ
ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ይህም ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት
ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x)
በምንስ ፡ ጀምሬ ፡ በምን ፡ ልጨርሰው
ጌታ ፡ ውለታህን ፡ በምን ፡ ቃል ፡ ልግለጸው
እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ክብርን ፡ አሰጥሃለሁ
በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊትህ ፡ እቀርባለሁ (፪x)
አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት
ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x)
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምህረትህ ፡ እጅግ ፡ በዝቶልኛል
ብዙ ፡ ኃጢአቴን ፡ ይቅር ፡ ብለኸኛል
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ፊትህ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት
ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x)
እኔም ፡ እንዳከብርህ ፡ አንተ ፡ መርጠኸኛል
በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ ደርበህልኛል
ሁልጊዜ ፡ በደስታ ፡ አዜምልሃለሁ
ራሴን ፡ ዝቅ ፡ በማድረግ ፡ አንተን ፡ አክብራለሁ (፪x)
አዝ፦ ሌላ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ አንተን ፡ የማከብርበት
ግን ፡ አንዲያው ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንደበት (፪x)
|