From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ክብር ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ስግደት ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ሙገሳ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሃሴትም ፡ አደርጋለሁ
የምሥጋና ፡ ቅኔን ፡ በፊትህ ፡ እቀኛለሁ (፪x)
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ሰይጣንን ፡ የረታ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ጸሎትን ፡ የሚሰማ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሃሴትም ፡ አደርጋለሁ
የምሥጋና ፡ ቅኔን ፡ በፊትህ ፡ እቀኛለሁ (፪x)
የምስኪኑ ፡ ወዳጅ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
የደሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ታማኝ ፡ ሚስጥረኛ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
በጽድቅ ፡ የተሞላ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሃሴትም ፡ አደርጋለሁ
የምሥጋና ፡ ቅኔን ፡ በፊትህ ፡ እቀኛለሁ (፪x)
እውነተኛ ፡ ጌታ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
እውነተኛ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
እውነተኝ ፡ አባት ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሃሴትም ፡ አደርጋለሁ
የምሥጋና ፡ ቅኔን ፡ በፊትህ ፡ እቀኛለሁ (፪x)
ሙገሳ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ሽብሸባ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
ጭብጨባ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ማነው ፡ ቢባል
ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሃሴትም ፡ አደርጋለሁ
የምሥጋና ፡ ቅኔን ፡ በፊትህ ፡ እቀኛለሁ (፪x)
|