አዜምለታለሁ (Aziemletalehu) - ታጋይ ፡ ወልደማርያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታጋይ ፡ ወልደማርያም
(Tagay Woldemariam)

Lyrics.jpg


(1)

ብዙ ፡ ዘመን ፡ የተሸከመኝ
(Bezu Zemen Yeteshekemegn)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታጋይ ፡ ወልደማርያም ፡ አልበሞች
(Albums by Tagay Woldemariam)

አዝ፦ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደወጣሁ ፡ ከጨለማ
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደገባኝ ፡ የአንተ ፡ አላማ

አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ፍቅር ፡ ሆኖ ፡ እንጂ
አይገባም ፡ ነበር ፡ ልትሆነኝ ፡ ወዳጅ
ይህንን ፡ እያሰብኩ ፡ ሁሌ ፡ አመልክሃለሁ
ጠላቴ ፡ እየሰማ ፡ ዘምርልሃለሁ) (፫x)

አዝ፦ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደወጣሁ ፡ ከጨለማ
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደገባኝ ፡ የአንተ ፡ አላማ

የሰላም ፡ ሃሳብ ፡ ነው ፡ የምታስብልኝ
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ እንዲሆንልኝ
እኔም ፡ ከፈቃድህ ፡ በፍፁም ፡ አልወጣም
ከአንተ ፡ ተለይቼ ፡ መኖር ፡ አልመኝም (፫x)

አዝ፦ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደወጣሁ ፡ ከጨለማ
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደገባኝ ፡ የአንተ ፡ አላማ

በሃጥያቴ ፡ ምክንያት ፡ ሞት ፡ ተፈርዶብኝ
ለሲኦል ፡ ለእሳት ፡ የታጨሁ ፡ ሳለሁኝ
አምላኬ ፡ ግን ፡ ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ስለበዛ
ከሞት ፡ አመለጥኩኝ ፡ ስለሆንከኝ ፡ ቤዛ (፫x)

አዝ፦ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደወጣሁ ፡ ከጨለማ
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደገባኝ ፡ የአንተ ፡ አላማ

ፍቅርህን ፡ በሞትህ ፡ ስለገለጽክልኝ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ በነጻ ፡ አገኘሁኝ
ክብሬን ፡ እያየሁ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለውን
አዜምልሃለሁ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ እያለኝ (፪x)
አዜምልሃለሁ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ እያለኝ

አዝ፦ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደወጣሁ ፡ ከጨለማ
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ አምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ነውና
እኔም ፡ ላክብርህ ፡ በዜማ ፡ እንደገባኝ ፡ የአንተ ፡ አላማ