From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ
ምሥጋናው ፡ ዘወተር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)
በጠዋት ፡ በማታ ፡ በቀን ፡ በሌሊት
ምሥጋናዬ ፡ ይድረስ ፡ ዘወትር ፡ በእርሱ ፡ ፊት
የአንደበቴን ፡ ፍሬ ፡ ከቶ ፡ አልቆጥብም
ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ አሃሃ ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ አልልም
አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ
ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)
የሕይወቴ ፡ ጋሻ ፡ ተገን ፡ ሆኖልኛል
ስወጣም ፡ ሰገባም ፡ እረፍቱ ፡ ከቦኛል
እርሱን ፡ ለማመስገን ፡ በገናዬን ፡ ላንሳ
ያደረገልኝን ፡ በፍፁም ፡ ሳልረሳ
አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ
ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)
ስላደረገልኝ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ
አመልከዋለሁኝ ፡ ሳልሰለች ፡ ለአንድ ፡ አፍታ
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምለው ፡ ምሰጠው ፡ የለኝም
ዘምርለታለሁ ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ
ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)
አቻምናን ፡ ማለፌ ፡ ሲደንቀኝ
አምናን ፡ በምህረትህ ፡ አለፍኩኝ
ለዘንድሮም ፡ ቢሆን ፡ አልፈራም
ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም (፫x)
ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም (፫x)
ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ ፡ ለነፍሴ
አድርገህላታል ፡ ኢየሱሴ (፪x)
አሳቤን ፡ ጭንቀቴን ፡ ወስደሃል
አምላኬ ፡ አሳርፈኸኛል
በሕይወቴ ፡ ልትኖር ፡ መርጠሃል
የእኔንም ፡ ምሥጋና ፡ ወድሃል (፪x)
የእኔንም ፡ ምሥጋና ፡ ወደሃል ፡ መርጠሃል ፡ መርጠሃል
የእኔንም ፡ አምልኮ ፡ መርጠሃል
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ ፡ ለነፍሴ
አድርገህላታል ፡ ኢየሱሴ (፮x)
|