From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ተአምር ፡ ሠሪው ፡ ተአምር ፡ ሠራ
እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እግዚአብሔር (፪x)
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ቃሉን ፡ ይፈጽማል
እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ ያስከብራል
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ
የማይጥል ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ
በሕይወቴ ፡ ውስጥ ፡ ክብሩን ፡ ስላየሁ
ታማኝነቱ ፡ ዛሬ ፡ አድርሶኛል
ለነገም ፡ ቢሆን ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል? (፬x)
አዝ፦ ተአምር ፡ ሠሪው ፡ ተአምር ፡ ሠራ
እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እግዚአብሔር (፪x)
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ቃሉን ፡ ይፈጽማል
እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ ያስከብራል
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ
አይረሳም ፡ እርሱ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ ያውቃል
በምድረ ፡ በዳ ፡ ሞገስ ፡ ይሆናል
ታማኙ ፡ ጌታ ፡ መድሃኒታችን
ኪዳን ፡ አክባሪ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታችን
አዝ፦ ተአምር ፡ ሠሪው ፡ ተአምር ፡ ሠራ
እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እግዚአብሔር (፪x)
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ቃሉን ፡ ይፈጽማል
እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ ያስከብራል
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ
በሰዎች ፡ ዕውቀት ፡ በሆነ ፡ ዝና
በምድር ፡ ጥበብ ፡ መች ፡ ይለካና?
የፍቅሩ ፡ ዕውቀት ፡ አዕምሮን ፡ ያልፋል
ተአምረኛ ፡ ነው ፡ ተአምር ፡ ሆኖናል
አዝ፦ ተአምር ፡ ሠሪው ፡ ተአምር ፡ ሠራ
እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እግዚአብሔር (፪x)
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ቃሉን ፡ ይፈጽማል
እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ ያስከብራል
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ቻይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ይሳነዋል?
በታላቅ ፡ ክንዱ ፡ ማስደነቅ ፡ ያውቃል
በአጋር ፡ ሠፈር ፡ ተአምር ፡ የሠራ
በእኛም ፡ መንደር ፡ ብርሃን ፡ አበራ!
አዝ፦ ተአምር ፡ ሠሪው ፡ ተአምር ፡ ሠራ
እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው
እግዚአብሔር (፪x)
ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ቃሉን ፡ ይፈጽማል
እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ስሙን ፡ ያስከብራል
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ
ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ
|