ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ (Siredagn Ayechewalehu) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝ፦ ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያግዘኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያቆመኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲመራኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
እስከ ፡ ዛሬ ፡ የረዳኸኝ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ የሆንኸኝ
በዝቶ ፡ ፀጋህ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
ሁሉ ፡ በአንተ ፣ መች ፡ በራሴ? (፬x)

የአምላኬ ፡ ምሕረቱ ፡ በዝቶልኝ
በቤቱ ፡ ዕድሜን ፡ ጨምሮልኝ
ለትላንት ፡ ስሰጋ ፡ የነበርኩ
አለሁኝ ፡ በጥላው ፡ ስለሆንኩ
የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያግዘኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያቆመኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲመራኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
እስከ ፡ ዛሬ ፡ የረዳኸኝ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ የሆንኸኝ
በዝቶ ፡ ፀጋህ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
ሁሉ ፡ በአንተ ፣ መች ፡ በራሴ? (፬x)

እጆቼን ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
ጉልበቴን ፡ በክብሩ ፡ አጽንቶ
መንፈሱን ፡ እጥፍ ፡ አድርጐልኛል
በክብሩ ፡ ክብሩን ፡ ገልጦልኛል
የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያግዘኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያቆመኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲመራኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
እስከ ፡ ዛሬ ፡ የረዳኸኝ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ የሆንኸኝ
በዝቶ ፡ ፀጋህ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
ሁሉ ፡ በአንተ ፣ መች ፡ በራሴ? (፬x)

ሲማማል ፡ ጠላቴ ፡ ሊጥለኝ
ቀንቶብኝ ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ
ቢወጣ ፡ ቢወርድ ፡ መች ፡ ይችላል?
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አጥር ፡ ሆኖኛል
የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያግዘኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያቆመኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲመራኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
እስከ ፡ ዛሬ ፡ የረዳኸኝ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ የሆንኸኝ
በዝቶ ፡ ፀጋህ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
ሁሉ ፡ በአንተ ፣ መች ፡ በራሴ? (፬x)

በሠልፉ ፡ እርሱ ፡ ተሰልፎ
ተዋጊው ፡ እግዚአብሔር ፡ አልፎ
የጠላት ፡ ከፍታው ፡ ተመቷል
ለሥሙ ፡ ምሥጋና ፡ ይገባል
የረዳኝን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ ሲረዳኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያግዘኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲያቆመኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
ሲመራኝ ፡ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ፡ ኢየሱስን
እስከ ፡ ዛሬ ፡ የረዳኸኝ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ የሆንኸኝ
በዝቶ ፡ ፀጋህ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
ሁሉ ፡ በአንተ ፣ መች ፡ በራሴ? (፬x)