ላመስግነው (Lamesgenew) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው

ይቅር ፡ ስላለኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌን
ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ በቃሁኝ ፡ እኔ
በቀን ፡ ውሎዬ ፡ ምሕረቱ ፡ በዝቶ
ስሙን ፡ እንዳስብ ፡ ሆነኝ ፡ መከታ

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው

ተከብቤያለሁ ፡ በእርሱ ፡ ቸርነት
ጠላቴ ፡ እንዳያይ ፡ በመግባት ፡ መውጣት
እጁን ፡ በላዬ ፡ ያወዛውዛል
ዛሬም ፡ ለነገ ፡ ምሕረቱ ፡ በዝቷል

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው

ልዘምርለት ፡ ስሙን ፡ ላክብረው
ወዶ ፡ ያዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ምሕረቱ ፡ እኔን ፡ ከቦኛልና
ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው

ኢየሱስ ፡ ምሕረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ናት
በእርሱ ፡ ሆነልኝ ፡ ወደ ፡ ዓብ ፡ መግባት
ከቶ ፡ አልታጣም ፡ ዘወትር ፡ ከፊቱ
ከቁጣው ፡ ይልቅ ፡ በዝቷል ፡ ምሕረቱ

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው

በፍርሃት ፡ ውስጥ ፡ በጭንቅ ፡ ተይዤ
የልቤን ፡ አምላክ ፡ ፊቱን ፡ ፈልጌ
ዘወር ፡ ብሎ ፡ መጣ ፡ እኔን ፡ አሰበኝ
ሥሙ ፡ ይባረክ! ፡ ፈጥኖ ፡ የታደገኝ

አዝላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፤ ይቅርታው