ላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት (Laderegelign Melkam Meheret) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝ፦ ስላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት
አልተፈረደብኝ ፡ አቤት ፡ ደግነት!
ተትቶልኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌ ፡ ሳይከፈለኝ
በቤቱ ፡ አለሁ ፡ ፀጋው ፡ ምሕረቱ ፡ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ፡ ላለው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
ክብር ፡ እሰጣለሁ ፡ ዛሬም ፡ ፊቱን ፡ አይቼ

እስቲ ፡ ልቁጠረው ፡ እርሱ ፡ ያደረገውን
ታላቅ ፡ ምሕረቱን ፡ የማይረሳውን
አሸጋገረኝ ፡ ምሕረቱ ፡ አሸጋገረኝ
አሸጋገረኝ ፡ ደግነቱ ፡ አሸጋገረኝ

አዝ፦ ስላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት
አልተፈረደብኝ ፡ አቤት ፡ ደግነት !
ተትቶልኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌ ፡ ሳይከፈለኝ
በቤቱ ፡ አለሁ ፡ ፀጋው ፡ ምሕረቱ ፡ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ፡ ላለው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
ክብር ፡ እሰጣለሁ ፡ ዛሬም ፡ ፊቱን ፡ አይቼ

እንዲህ ፡ የማረከኝ ፡ የእርሱ ፡ ምሕረት
ሁሌ ፡ ያኖረኛል ፡ በቤቱ ፡ በዕውነት
አልዘነጋውም ፡ ቸርነቱን ፡ አልዘነጋውም
አልዘነጋውም ፡ በጐነቱን ፡ አልዘነጋውም

አዝ፦ ስላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት
አልተፈረደብኝ ፡ አቤት ፡ ደግነት!
ተትቶልኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌ ፡ ሳይከፈለኝ
በቤቱ ፡ አለሁ ፡ ፀጋው ፡ ምሕረቱ ፡ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ፡ ላለው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
ክብር ፡ እሰጣለሁ ፡ ዛሬም ፡ ፊቱን ፡ አይቼ

የማያልቅ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ምሕረት
ከዕለት ፡ ወደ ፡ ዕለት ፡ ዕረፍት ፡ የሚሰጥ
የማያልቅ ፡ ነው ፡ ምሕረቱ ፡ የማያልቅ ፡ ነው
የማያልቅ ፡ ነው ፡ ቸርነቱ ፡ የማያልቅ ፡ ነው

አዝ፦ ስላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት
አልተፈረደብኝ ፡ አቤት ፡ ደግነት!
ተትቶልኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌ ፡ ሳይከፈለኝ
በቤቱ ፡ አለሁ ፡ ፀጋው ፡ ምሕረቱ ፡ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ፡ ላለው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
ክብር ፡ እሰጣለሁ ፡ ዛሬም ፡ ፊቱን ፡ አይቼ

ጽድቅ ፡ የለኝ ፡ እኔ ፡ የምመካበት
በቤቱ ፡ መኖር ፡ የምችልበት
ምሕረቱ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ለእኔ ፡ ምሕረቱ ፡ ነው
በጐነቱ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ለእኔ ፡ በጐነቱ ፡ ነው

አዝ፦ ስላደረገልኝ ፡ መልካም ፡ ምሕረት
አልተፈረደብኝ ፡ አቤት ፡ ደግነት!
ተትቶልኝ ፡ ብዙ ፡ በደሌ ፡ ሳይከፈለኝ
በቤቱ ፡ አለሁ ፡ ፀጋው ፡ ምሕረቱ ፡ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ፡ ላለው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
ክብር ፡ እሰጣለሁ ፡ ዛሬም ፡ ፊቱን ፡ አይቼ