ከአንተ ፡ በቀር (Kante Beqer) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም
ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም

ይዘመርልህ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነህ

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የተከበረ?
በኃይሉ ፡ ሥልጣን ፡ ያልተደፈረ
ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ዛሬም ፡ ደግሞ ፡ ያለው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ሥሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
አልተለወጠም ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ብርቱ ፡ አምላክ ፡ ነው

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም
ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም

ምሕረት ፡ ዕውነቱ ፡ የተገለጠ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ያልተለወጠ
ዕውነቱ ፡ ከምድር ፡ እስከ ፡ ሰማይ ፡ ያለው
ሰላምን ፡ ለሕዝቡ ፡ ሁሌ ፡ የሚናገረው
ያየነው ፡ ዕውነት ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ተወዳዳሪ ፡ ምን ፡ መሳይ ፡ አለው?

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም
ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም

ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማን ፡ ብርቱ ፡ አለ?
ሳይሰጋ ፡ ከቶ ፡ በክብር ፡ ያለ
በተዘረጋ ፡ ክንዱ ፡ ሁሉን ፡ በሚችለው
ተአምራት ፡ በመሥራት ፡ ስሙን ፡ ያስከበረው
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው
ኃያል ፡ ሥም ፡ ያለው ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም
ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም