እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ አላገኘሁም (Ende Esu Yale Alagegnehum) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ አላገኘሁም
ብወጣ ፡ ብወርድ ፡ ከቶ ፡ አላየሁም
የሚደግፍ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያቆም ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ማንን ፡ ጥሎ ፡ እርሱ ፡ ያውቃል
ለሚጠሩት ፡ ፈጥኖ ፡ ይደርሳል
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ለሁሉ ፡ ይበቃል (፪x)

እርሱን ፡ የታመነ ፡ በመንገዱ ፡ ሁሉ
አይወድቅም ፡ ዘለዓለም ፡ ያቆመዋል ፡ ቃሉ
በጨለማው ፡ ዓለም ፡ ብርሃን ፡ እየሆነው
ይመራዋል ፡ ጌታ ፡ ቅጥር ፡ እያዘለለው

ከጠላት ፡ ተናጥቀህ ፡ ለዚህ ፡ ያበቃኸን
ኃይልህንም ፡ ልከህ ፡ እኛን ፡ የረዳኸን
በመንገዳችን ፡ ላይ ፡ ቸርነት ፡ አድርገሃል
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

አያስፈልግ ፡ ሌላ ፡ ሁልጊዜ ፡ በቂ ፡ ነህ
ዘወትር ፡ ከለላ ፡ ድጋፍ ፡ መመኪያ ፡ ነህ
አንተን ፡ የተጠጋህ ፡ የተማጸነህ ፡ ሰው
የጠላትን ፡ ሰፈር ፡ አተረማመሰው

አመልን ፡ አዋቂ ፡ ገበናን ፡ ሸፋኝ ፡ ነህ
አንተ ፡ የናዝሬት ፡ ሰው ፡ ዘወትር ፡ መልካም ፡ ነህ
ሁሉን ፡ እንደ ፡ ዓመሉ ፡ ችለህ ፡ ታኖራለህ
አትለወጥ ፡ አንተ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ያው ፡ ነህ